ዘ ስሊስታክ ጎድ

ከውክፔዲያ

ዘ ስሊስታክ ጎድ (እንግሊዝኛThe Sleestak God፣ «የስሊስታኩ ጣኦት») በመስከረም ፬ ቀን 1967 ዓም (1974 እ.ኤ.አ.) ቅዳሜ ጥዋት የተሠራጨ ትርዒት ሲሆን በተከታታይ ፊልም ላንድ ኦቭ ዘ ሎስት («የጠፉት ሀገር»፤ በሲድና ማርቲ ክሮፍት ተዘጋጅቶ) ፩ኛው ምዕራፍ ፪ኛው ትርዒት ነበር።

በፊልሙ ልቦለድ ውስጥ፣ ሦስት ጀብደኞች ተጓዦች፣ አንድ አባትና ሁለት ልጆቹ በምስጢርም ሆነ በተዓምር በፍጹም ወደ ሌላ ዓለም ወይም ፈለክ ደርሰዋል። በዚሁም ዓለም ሌሎች ፍጡሮች አሉ። «ፐኩኒ» የተባለ ጦጣ ወይም ሰው መሳይ ዝርያ አለ፣ ከነርሱም «ቻ-ካ» የተባለ ግለሠብ ያገኛሉ። እንዲሁም ኃያል እንሽላሊት አይነቶች በዚህ ዓለም ይኖራሉ።

ልጆቹና ቻ-ካ በአንድ ፍርስራሽ ደርሰው «ከ ስሊስታክ ተጠንቀቁ!» የሚል ምልክት አዩ። ወድያው ቻ-ካ በቋንቋው «ሰሪሰታከ!» ብሎ ይጮህ ጀመር፣ ወደ ጫካ ሸሸ። ። ከትንሽ በኋላ ሶስት ረጅም እንሽላሊት መሳይ ፍጡሮች ወይም «ስሊስታክ» ታይተው ልጆቹን ይይዙዋቸዋል። በመጨረሻ ግን በአባታቸውና ቻ-ካ ርዳታ ልጆቹ እንደ ስሊስታኮች መስዋዕት ሳይሰዉ ያመልጣሉ።