Jump to content

የሆር-ለቫል ውል

ከውክፔዲያ
(ከየሆዋሬ-ለቫል ውል የተዛወረ)

የሆር ላቫል ውል በ 1935 ታህሣስ ወር ላይ በብሪታንያ የውጪ ጉዳይ ፀሃፊ በነበረው ሣሙኤል ሆር እና በፈረንሣይ ጠቅላይ ሚኒስተር ፒየር ላቫል ተዘጋጅቶ ቀረበ። የዚህ ውል አላማው በጊዜው የነበረውን ኢጣሊዮ-አቢሢኒያ ጦርነት ለመደምደምና በ1896 በተደረገው ጦርነት ተዋርዶ የተሸነፈውን አቢሲንያን በመክፈል ለመቀበል ነበረ።

ጣሊያን አምባገነን መሪ የነበረው ቤኒቶ ሙሶሊኒ አላማ የነበረው ግን አቢሲንያን ነጻ አድርጎ በጣልያን መንደር ግዛት ስር ማድረግ ነበረ። ይህ የቤኒቶ ሞሶሎኒ ሀሳብ ግን በብሪቴን እና ፈረንሳይ ላይ ጥላች ያለው አሰተሣሠብን አስነሳ። ቢሆንም ግን ይህ ጥላቻ የተሞላበት አሰተሣሠብ ለውጥ ማምጣት አልቻለም ነበር ሆኖም ለውጥ ማምጣት ያልቻሉት ብሪቴን እና ፈረንሳይ ጣሊያንን ከእነሱ ጋር በአዶልፍ ሂትለር ምኞት እና ፍላጎት ላይ እንደገና ከእነሱ ጋር እንድትተባበር ቢፈልጉም ከዚህ በላይ ግን ሞሦሎኒ በጣርነቱ ጌዜ ጀነራሉ ማርሻል ከሚሊኦ ደካማ አፈፃፀም እና ያልተጠበቀው የአቢሲኒያዎች የመካከል ብቃት ምክኒያት የተነሣ ሞሦሎኒ የአቢሲኒያ ጦርነት መደምደም ፈለገ።[1]

ይህ ውል በለንደን የሚገኘው የጣሊያን አምባሣደር የሆነው ዲኖ ግራንዲ እና ቆሚ የውጪ ጉዳይ ቢሮ ፀሀፊ የነበረው ሮበርት ቫንስታርት የተደረገ ድርድር ወይም ስምምነት ነበር። የቫንስታርት ጭንቀት ግን የነበረው የብሪቲሽ የመከላከል ድክመት እና በ[[ሜዲትራኔያን፤ ግብፅ እና መካከለኛ ምሥራቅ ላይ የነበረው ቦታ ነበር ፍርሃቱ የነበረው ደግሞ ናዚ ጀርመን ነበረች። ከውሉ ውስጥ ጣሊያን የኦጋዴንን እና የትግራይን የቀረበውን ክፍል ለማግኘት እና ኢኮኖሚካል ተሠሚነቱን ለአቢሲንያ ደቡባዊ ክፍል እንዳለ ማስፋት እና ወደ በሀሩ ለመሄድ ዋስትና ያለው መተላለፊያ አሠብ ላይ እንዲያገኙ ነበር። ሞሦሎኒ ለመስማማት ዝግጁ ሆኖ እንደል ለህዝብ ይፋ ለማውጣት ግን ዘገይቶ ነበር። ስምምነቱ በብሪቴን ውስጥ ትልቅ ንቅናቄን በተቋሚዎች ላይ አሰከተለ ታህሳስ 10 ላይ ተቋሚ የነበረው አንዱ ሠራተኛ ድርጅት ጥያቄ አነሣ ጋዜጣው ዘገባ እውነት ከሆነ መንግስት የማህበር መምሪያ እያፈረሰ ድጋፍ እያሠጣ ነው በማለት በተካሄደው ምርጫ ላይ ለማሸነፍ ችለዋል።[2]

  1. ^ http://www.britannica.com/EBchecked/topic/268400/Hoare-Laval-Pact
  2. ^ http://ww2db.com/battle_spec.php?battle_id=158