Jump to content

የኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር

ከውክፔዲያ

በዘመነ ኢህአዴግ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

(ወደፊት ገስግሺ ውድ እናት ኢትዮጵያ)

የዜግነት ክብር በኢትዮጵያችን ፀንቶ
ታየ ህዝባዊነት ዳር እስከዳር በርቶ
ለሰላም ለፍትህ ለህዝቦች ነፃነት
በእኩልነት በፍቅር ቆመናል ባንድነት
መሰረተ ፅኑ ሰብዕናን ያልሻርን
ህዝቦች ነን ለስራ በስራ የኖርን
ድንቅ የባህል መድረክ ያኩሪ ቅርስ ባለቤት
የተፈጥሮ ፀጋ የጀግና ህዝብ እናት
እንጠብቅሻለን አለብን አደራ
ኢትዮጵያችን ኑሪ እኛም ባንቺ እንኩራ።

1984 ዓ.ም፣ ዘመነ ኢህአዴግ

በዘመነ ደርግ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ -ኢትዮጵያ ቅደሚ
በኅብረተሰባዊነት - አብቢ ለምልሚ!
ቃል ኪዳን ገብተዋል - ጀግኖች ልጆችሽ
ወንዞች ተራሮችሽ - ድንግል መሬትሽ
ለኢትዮጵያ አንድነት - ለነፃነትሽ
መስዋዕት ሊሆኑ - ለክብር ለዝናሽ!
ተራመጂ ወደፊት - በጥበብ ጎዳና
ታጠቂ ለሥራ - ላገር ብልጽግና!
የጀግኖች እናት ነሽ -  በልጆችሽ ኩሪ
ጠላቶችሽ ይጥፉ - ለዘላለም ኑሪ።

1968 ዓ.ም፣ ዘመነ ደርግ

በንጉሱ ዘመን

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

(ማርሽ ተፈሪ)

ኢትዮጵያ ሆይ ደስ ይበልሽ
በአምላክሽ ኃይል በንጉስሽ
ተባብረዋልና አርበኞችሽ
አይነካም ከቶ ነፃነትሽ
ብርቱ ናቸውና ተራሮችሽ
አትፈሪም ከጠላቶችሽ።
ድል አድራጊው ንጉሣችን 
ይኑርልን ለክብራችን።

1919 ዓ.ም፤ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት (አጼ ቀደማዊ ኃይለ ሥላሴ)