የእንቦጭ አረም

ከውክፔዲያ
የእንቦጭ አረም

የእንቦጭ አረም (Eichhornia crassipes) በጣም አስቸጋሪ የሆነ፣ በውሃ ላይ የሚበቅል ወራሪ አረም ነው።

በጣም ቶሎ ሊስፋፋ ይችላል። ይህ ማለት በየ፪ ሳምንት ውስጥ መጠኑ ሊደረብ ይችላል። ኩሬ ወይም ሃይቅ ሲሸፈን፣ ጸሓይን ወይም ሌሎችን አትክልት፣ አሦችን ይክለክላል፤ ለትንኝ እና ለብዙ ተላላፊ በሽቶች መኖሪያ ይሆናል። ከሌሎቹ በሽቶች በላይ አረሙ እከክ መፍጠር ይችላል።

በመጀመርያ ለደቡብ አሜሪካ ኗሪ ነበር። ዛሬ ግን ወደ ኒው ዚላንድፓፑዋ ኒው ጊኒካምቦዲያሉዊዚያና ክፍላገር አሜሪካኬረለ ክፍላገር ሕንድ፣ እና በቪክቶሪያ ሀይቅ አፍሪካ፣ ኢትዮጵያማላዊግብጽ ወርሮ ትልቅ ችግር ሆኗል።

እፃዊ ተዋልዶ በፍጥነት ማባዛት ስለሚችል፣ ትንንሽ ክፍሎች ቢሆኑም በውሃው ውስጥ ቢቀሩ፣ ዳግመኛ ውረት ሊሆን ይችላል።

በአንዳንድ አገር ውስጥ፣ እንቦጭን የሚበሉ የነቀዝ ዝርያዎች እና የብል፣ የፌንጣ ዝርያ እንዲበሉት አስገብተዋል።

ጉማሬ የእንቦጭ አረም እንዲበላ በማሠብ፣ በ1902 ዓም ጉማሬዎችን ወደ ሉዊዚያና ለማስገባት የሚል ሀሣብ በአሜሪካ ምክር ቤት ቀረበ፣ ሆኖም እንደ ሕግ መቸም አልተቀበለም።

ጥቅሞች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

አረሙ በበዛ ጊዜ አስቸጋሪ ሲሆን፣ አንዳንድ ጥቅሞ አለው።

  • በሕንድ አገር፣ ከውሃው አውጥተውት፣ ከደረቀ በኋላ ለማገዶ ይጠቀማል፤ አመዶችም አፈርን ለማዳበር ይጠቅማሉ።
  • የአረሙ ባህርይ ውሃውን ከብዙ በካዮች ይጠራል። ስለዚህ የቆሻሻ ውሃን (በተለይ በወተት ርቢ ቤት) ለማከም ሆን ብሎ ታርሷል።
  • ታይዋንና በጃቫ ደሴት ኢንዶኔዥያ፣ ተበስሎ እንደ ምግብ ይበላል።
  • ከዳህማሌዥያ፣ የአበባው ውጥ የፈረስን ቆዳ ለማከም ይጠቀማል።
  • በቪክቶሪያ ሐይቅ ዙሪያ፣ ገመድ፣ የእጅ ቦርሳ፣ ሌሎችም እቃ ይሠራበታል።
  • አንዲት ናይጄሪያዊት ባለድርጅት አቸንዮ ኢዳቻባ ከተክሉ የእጅ ሥራዎች በመሥራት ትርፍን ለማትረፍ ቻለች - «ከገዳይ አረም ወደሚያተርፍ ንግድ ቀየርኩ» - ቪዴኦ (ድረ ገጽ ቢዘገይ በዩቱብ ይዩት እዚህ)