የወባ ትንኝ

ከውክፔዲያ
(ከትንኝ የተዛወረ)
?የወባ ትንኝ
የቢጫ ወባ ቢንቢ ሰውን ስትነክስ
የቢጫ ወባ ቢንቢ ሰውን ስትነክስ
ሳይንሳዊ ደረጃ መስጫ
ስፍን: እንስሳ
ክፍለስፍን: ጋጥመ-ብዙ
መደብ: ሦስት አጽቄ
ክፍለመደብ: ዝምብ Diptera
ንኡስ ክፍለመደብ: ትንኝ Nematochera
Infraorder: Culiomorpha
ልእለ አስተኔ: Culicoidea
አስተኔ: የወባ ትንኝ Culicudae

የወባ ትንኝ ወይንም ቢንቢዝንብ አይነት እንስሳ ናት። የትንኝ ሴቶች ተዋህስያን ስለሆኑ በደመ ሙቅ እንስሳት ላይ አርፈው፣ የእንስሳውን ቆዳ በሹል አፋቸው ከበሱ በኋላ፣ ምራቃቸውን ይረጩበታል። ይህን እሚያደርጉት የበሱት እንስሳ ደም እንዳይረጋ ነው። በእዚህ ሁኔታ ነገሮችን ካመቻቹ በኋላ፣ የአረፉበትን እንስሳ ደም ይመገባሉ ማለት ነው።

በሽታ የሚያጋቡት፣ ቆዳ ሲበሱ ወይንም ደም ሲመጡ ሳይሆን፣ ምራቃቸውን ሲረጩ ነው። ለእዚህ ምክንያቱ በምራቃቸው ውስጥ አደገኛ ተውሳኮች ጎጆአቸውን ቀልሰው ስለሚኖሩ ነው[1][2] ። በመገቡበት ቦታ ላይ እከክ የተነሣበት ምክንያት ምራቃቸው ቆዳውን ስለሚያሳውከው ነው።

ወንዶች ትንኞች የአበባ ጣዝማ ነው ምግባቸው። ሴቶቹም እንዲሁ የአበባ ጣዝማ ይመገባሉ፣ ሆኖም እንቁላል ሊጥሉ ሲሉ ብዙ ፕሮቲን ስለሚያስፈልጋቸው፣ የግዴታ ደም መምጠጥ አለባቸው። አለበለዚያ እንቁላል መጣል አይችሉም።



ማጣቀሻ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ Harrison, Gordon A. 1978. Mosquitoes, malaria, and man: a history of the hostilities since 1880 ISBN 0525160256 / 0-525-16025-6
  2. ^ Day, Nancy 2001. Malaria, West Nile, and other mosquito-borne diseases Enslow. ISBN 9780766015975