የዊሶን ሽክርክረ ነፋስ

ከውክፔዲያ

የዊሶን ሽክርክረ ነፋስአውስትራሊያዊው ሳይንስ ሊቅ ዶ/ር ማክስ ዊሶንውኃ መፍጠሪያ ፈጠራ ነው።

ይኸው ፈጠራ ንጹሕ፣ የሚጠጣ ውኃከባቢ አየር ማውጣት ይችላል። ይህ የሚቻለው በቅዝቃዛ ማራገቢያ ነው። ማራገቢያው ከአየሩ ይልቅ ቅዝቃዛ ስለ ሆነ፣ በከባቢው አየር በሰፊ የሚገኘው የውሃ እንፋሎት ወደ ፈሳሽነት ይለወጣል። ይህም እንኳን በድርቅ አገር ወይም በበረሃ ይሠራል። የዊሶንም መሳሪያ በአንድ ቀን ውስጥ 10,000 ሊተር ንጹሕ ውኃ ማስገኘት ስለሚችል[1]፣ «ምድረ በዳ ወደ ገነት ሊቀይር ይችላል» የሚል ተስፋ አለ።

ዶ/ር ዊሶን እንዳለ፣ «በአየሩ ውስጥ የሚገኘው ውኃ መጠን ለተግባራዊ ምክንያት ሁሉ ያልተወሰነ ነው። (በከባቢ አየር) ታችኛው 1 ኪሎሜትር ለብቻው 1,000,000,000,000,000 ያህል ሊተር ውሃ አለበት፣ ያውም በጥቂት ሰዓት ውስጥ ይገለበጣል። 'የዊሶን ሽክርክረ ነፋስ' ወይም 'የማክስ ውኃ ከአየር መፍጠሪያ' የትም ቦታ፣ ምንጊዜም፣ ድርቅ ቢኖርም ባይኖርም፣ በቂ ውኃ ማስገኘት ያስችላል።»

ከዚህ በላይ፣ «ተለይተው የሚኖሩ ደረቅ ኅብረተሠቦች፣ በእርግጥ፣ ለኑሮ ሰዎች የውኃ ጋን በራሳቸው ላይ መሸከም አስፈላጊነት ያለባቸው ቦታዎች፣ ሊቀየሩ ይቻላል፤ የኛም አዲስ ትንሽ ድርጅት ለነዚህ ችግረኛ ኅብረተሠቦች ከመጀመርያዎቹ መሳርያዎቹ አንዳንዱን ለማድረስ ኃላፊነት አለው» ብሏል።

  1. ^ "HowStuffWorks - Creating Water from Thin Air" (እንግሊዝኛ)