ዱለት

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

ዱለት ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰራ የምግብ አይነት ሲሆን፣ የሚሰራውም ከጉበትጨጓራ ነው።

አዘገጃጀት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

አስፈላጊ ነገሮች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

1 lb. ጨጓራ (የበግ)
1 lb. ጉበት (የበግ)
1 lb. የተፈጨ የበሬ ስጋ (ቀይ)
1 ማንኪያ ቀይ በርበሬ
3 መካከለኛ አረንጓዴ የተከተፉ ቃሪያወች
1/3 የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት
1 ኩባያ የተነጠረ ቅቤ
ስድስት የሚሆን ፓርስሊ
4 እገር ነጭ ሽንኩርት በደምብ የተከተፉ

ዝግጅት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ጨጓራውንና ጉበቱን በሚፈስ ውሃ በደንብ አድርገው ያጽዱ። ከዚያም ጨጉዋራውን፣ ጉቤቱን ለየብቻ በጥቃቅን ከከተፉ በኋላ ከተፈጨው ስጋ ጋር ለያይተው ፣ በመጥበሻ (ማንከሽከሻ) ያለምንም ቅቤ ወይም ዘይት ይጥበሱ ( ጨጉዋራ ለብቻ፣ ጉበት ለብቻ፣ ስጋ ለብቻ)። ከዚያ በማደባለቂያ (ብሌንደር) ፓርስሊውን፣ ነጭ ሽንኩርቱንና ቃሪያውን ያደባልቁ። ከዚያ በሰፊ ጎድጘዳ ሳህን ፣ ከበርበሬ ጋር ይደባልቁ። ንጥር ቂቤውን በዚህ ላይ ካፈሰሱ በኋላ፣ የበሰሉትንም ስጋወች ከመጥበሻቸው አውጥቶ አንድ ላይ ከዚህ ጋር በመደባለቅ ስራው ይጠናቀቃል።

መልካም ዱለት!!!