ድጉና ፋንጎ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

ድጉና ፋንጎ ወላይታ ዞን ከሚገኙ ወረዳዎች አንዱ ነው። ወረዳው በስተደቡብ ምዕራብ በዳሞት ወይዴ፥ በስተሰመን ምዕራብ ዳሞት ጋሌ በስተምሥራቅ በሲዳማ ክልል፥ በስተሰሜን በሀዲያ ዞን እንዲሁም ደግሞ በበስተደቡብ በአበላ አባያ ወረዳ ይዋሰናል።

የህዝብ ቁጥር[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በ1999 ዓ.ም በማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ በተደረገው ህዝብ ቆጠራ መሰረት በወረዳው በአጠቃላይ 96,480 ሰው የሚኖር ሲሆን፥ ከነዚህም 47,493 ወንድ ሲሆኑ 48,987 ደግሞ ሴት ናቸው፤ ከ3,400 የሚበልጡ ማለትም 3.53% የምሆኑት በከተማ ይኖራሉ። ወላይታ ዲምቱ , ቢጠና እና ቀርጨጬ ዋነኞቹ የወረዳዉ ከተሞች ናቸው።[1] የሚበዙት የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ሲሆኑ፥ 84.43% ያህሉን ይይዛሉ፤ 8.97% የሚሆኑት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያን እና 5.57% የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታይ ናቸው።[2]

ዋቢ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ "Admirative Map of SNNPR". በ6 October 2020 የተወሰደ.
  2. ^ Census 2007 Tables: Southern Nations, Nationalities, and Peoples' Region Archived ኖቬምበር 13, 2012 at the Wayback Machine, Tables 2.1, and 3.4.