የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ

ከውክፔዲያ

የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ (ማ.ስ.ኤ.) በኢትዮጵያ መንግሥት በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ስር የሚገኝ ኤጀንሲ ወይም ባለስልጣን ሲሆን ተልዕኮው ለኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ዕድገት አሰሳ የሚያገለግሉ የሕዝብ ቆጠራ፣ የዋጋ መረጃ ማሰባሰብ፣ የቤተሰብ ፍጆታና ወጪን ማጥናትና ሌሎች ተመሳሳይ ተግባሮችን ማከናወን ነው። በተጨማሪም ኤጀንሲው በዘርፉ ባለሙያዎችን የማሰልጠን ኃላፊነት አለበት። በአሁኑ ጊዜ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ሳሚያ ዘካሪያ ናቸው።

ከየካቲት ፴ ቀን ፲፱፻፹፩ ዓ.ም. በፊት ኤጀንሲው የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ቢሮ በመባል ይታወቅ ነበር። በአሁኑ ጊዜ ኤጀንሲው በሚከተሉት ፳፭ ቦታዎች ቅርንጫፎች አሉት፦ አዲስ አበባአምቦአርባ ምንጭአሰበ ተፈሪአሳይታአሶሳአዋሳባህር ዳርደብረ ብርሃንደሴድሬ ዳዋጋምቤላእንደ ሥላሴጋምቤላጎባጎንደርሐረርሆሳዕናጅጅጋጅማመቀሌሚዛን ተፈሪናዝሬትነገሌነቀምት እና ሶዶ[1]

አገር አቀፍ የሕዝብና መኖሪያ ቆጠራ እ.ኤ.አ. በ1984፣ 1994፣ 2007 የተከናወነ ሲሆን የመጨረሻዎቹ ሁለት ቆጠራዎች ዝርዝር መረጃ በኤጀንሲው ድረ-ገጽ ላይ ይገኛል።

ማመዛገቢያ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ "Branch offices" Archived ኦገስት 16, 2010 at the Wayback Machine, Central Statistical Agency website (በነሐሴ ፯ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. የተወሰደ) (እንግሊዝኛ)

ደሳለ

የውጭ መያያዣ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]