ጀድኸፐረው

ከውክፔዲያ
ጀድኸፐረው
ይህ «የኦሲሪስ አልጋ» የተባለው ቅርስ በጀድኸፐረው ዘመን በጥንታዊ ፈርዖን ጀድ መቃብር ገባ።
ይህ «የኦሲሪስ አልጋ» የተባለው ቅርስ በጀድኸፐረው ዘመን በጥንታዊ ፈርዖን ጀድ መቃብር ገባ።
የግብጽ ፈርዖን
ግዛት 1781 ዓክልበ. ግ.
ቀዳሚ ሰኸምሬኹታዊ ኻውባው
ተከታይ ሰጀፋካሬ
ሥርወ-መንግሥት 13ኛው ሥርወ መንግሥት
አባት ሆር አዊብሬ?

ጀድኸፐረው ላይኛ ግብጽ2ኛው ጨለማ ዘመን (13ኛው ሥርወ መንግሥት) ለአጭር ጊዜ በ1781 ዓክልበ. ግድም የገዛ ፈርዖን ነበረ። የሰኸምሬኹታዊ ኻውባው ተከታይ ነበረ።

ስሙ በቶሪኖ ቀኖና ነገሥታት ዝርዝር ላይ የለም። ሆኖም ከሥነ ቅርስ ረገድ ፈርዖንነቱ እርግጥኛ ነው። ስሙ ከቶሪኖ ዝርዝር ጠፍቶ የኻውባው ተከታይና ወንድም እንደ ነበር ይታስባል፤ በ«ኦሲሪስ አልጋ» በተባለው ቅርስ ላይ ሌላ ስሙ (የአባት ስም) «ሆር» (ሆር አዊብሬ) እንደ ነበር ይመስላል። በተጨማሪ የጀድኸፐረው ስም በ፲፩ ማኅቴሞች ላይ በአባይ ፪ኛው ሙላት አካባቢ (በኩሽ መንግሥት ጠረፍ) ሲገኝ ማኅተሞቹ ከቀዳሚው ከኻውባውና ከታችኛው ግብጽ ፈርዖን ከሸሺ ማዓይብሬ ማኅተሞች አጠገብ ተገኙ።

የጀድኸፐረው ተከታይ ሰጀፋካሬ (ካይ-አመነምሃት) ምናልባት ልጁ ነበር።

ቀዳሚው
ሰኸምሬኹታዊ ኻውባው
ግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን
1781 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ሰጀፋካሬ

ዋቢ ምንጭ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  • K.S.B. Ryholt: The Political Situation in Egypt during the Second Intermediate Period, c. 1800 – 1550 BC, Carsten Niebuhr Institute Publications, vol. 20. Copenhagen: Museum Tusculanum Press, 1997 (እንግሊዝኛ)