ጥር ፮
Appearance
(ከጥር 6 የተዛወረ)
ጥር ፮ ቀን፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፳፮ ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ዮሐንስ ፪፻፵ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ማቴዎስ፤ ማርቆስ እና ሉቃስ ደግሞ ፪፻፴፱ ዕለታት ይቀራሉ።
፲፱፻፵፫ ዓ.ም. ብጹዕ አቡነ ባስልዮስ (የቀድሞው እጨጌ ገብረ ጊዮርጊስ በካይሮ ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ከእስክንድርያው ፓትርያርክ መዓርገ ጵጵስና ተቀብለው የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ኾነው ተቀቡ። ነገር ግን የፓትርያርክነቱን ማዕርግ የእስክንድርያው ፓትርያርክ ከሞቱ በኋላ ሰኔ ፳፩ ቀን ፲፱፻፶፩ ዓ/ም ነው የተሰጡት።
- ሪፖርተር፣ ኪንና ባህል - “ሳምንቱ በታሪክ”