ፍኖተ ሰላም

ከውክፔዲያ

የፍኖተሰላም ከተማ የምትገኘው በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምዕራብ ጎጃም ዞን ጃቢጠህናን ወረዳ ከአዲስ አበባ በ 387 ኪ.ሜ ከክልሉ ዋና ከተማ ባህርዳር ደግሞ 176 ኪ.ሜ ላይ ነው፡፡ አስትሮኖሚያዊ መገኛ ቦታዋም በ10º 41’ ሰሜን ላቲቲውድ እና 37º 16’ ምስራቅ ሎንግቲውድ ነው፡:1 ፍኖተ ሰላም (ፍ/ሰላም) በኢትዮጵያ ውስጥ በጎጃም እምብርት ላይ የምትገኝ ከተማ ናት።

አመሰራረት

ፍኖተሰላም ከተማ የተቆረቆረችው በ 1933 ዓም ነው፡፡ፍኖተሰላም በክልሉ ከሚገኙ የሪፎርም ከተሞች ስትሆን፣ የከተማ አስተዳደር፣ ማዘጋጃ ቤት፣ 3 የከተማና 2 የገጠር ቀበሌዎች አላት፡፡ በ2003 ዓ.ም የተዘጋጀ መዋቅራዊ ፕላንም አላት፡፡ ፍኖተ ሰላም ማለት መልካም መንገድ ወይም ጉዞ እንደማለት ሲሆን ይህንንም ስም ያወጡላት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ እንደሆኑ ይነገራል። ጃንሆይ ከጣሊያን ጦርነት በኋዋላ ከስደት ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ አሁን ፍኖተ ሰላም ያለችበት ቦታ ላይ ከአጃቢዎቻቸው ጋር እረፍት ያደርጋሉ። እስከዚያን ጊዜ ድረስ ያደረጉት ጉዞም በሰላም የተሞላ ስለነበር ያንን ቦታ ፍኖተ ሰላም ብለው ሰየሙት። ከከተማዋ ወጣ ብሎ የሚገኝ አንድ የዋርካ ዛፍ ይገኛል። ይህንንም የዋንዛ ዛፍ የተከሉት ንጉሱ ስለነበሩ እስካሁን ድረስ የአባ ንጉስ ዋንዛ እየተባለ ይጠራል።

ፍኖተ ሰላም በብዙ ነገር ትታወቃለች። በአካባቢው ያሉ ገበሬዎች ጤፍበቆሎዳጉሳኑግበርበሬ እና ሌሎችንም የእህል አይነቶች ያበቅላሉ። በፍራፍሬ ሎሚብርቱካንፓፓዬ እንደልብ ይገኛል። በጣም ጥራት ያለው ቡና የሚገኝባት አገር ናት - ፍ/ሰላም። የባከል ቡና በጣዕሙ ይታወቃል። ከከተማው ወጣ ብሎ የገራይ የውሃ ግድብ ስለሚገኝ በተለይ በፆም ጊዜ እጅ የሚያስቆረጥም አሳ ይገኛል። ፍ/ሰላም በወተትና በማር ሀብትም በጣም የታውቀች ከተማ ናት። በከተማዋ አንድ ሁለተኛ ደረጃና አንድ መሰናዶ ትመሀርት በቶች አንዲሁም አንድ መምህራን ማሰልጠኛ ኮለጅ ይግኛሉ።reference 1 http://www.mwud.gov.et/web/finoteselam/home Archived ማርች 20, 2015 at the Wayback Machine