Jump to content

፩ኛ ወደ ቆሮንጦስ ፪

ከውክፔዲያ
፩ኛ ወደ ቆሮንጦስ ፪
በ፫ኛው ክፍለ ዘመን የተጻፈ ፩ኛ ወደ ቆሮንጦስ ፪:፫-፲፩ ገጵ ፸፰ በፓፒረስ ፵፭

ቅዱስ ጳውሎስ
ቅዱስ ጳውሎስ በዕሥር ቤት መልዕክቱን ሲያስተላልፍ
አጭር መግለጫ
ፀሐፊ ጳውሎስ
የመጽሐፍ ዐርስት ፩ኛ ወደ ቆሮንጦስ
የሚገኘው በአዲስ ኪዳን ፯ኛው መጽሐፍ
መደብ የጳውሎስ መልዕክት


፩ኛ ወደ ቆሮንጦስ በአዲስ ኪዳን ሁለተኛው መልዕክት ሲሆን ቅዱስ ጳውሎስ በቆሮንጦስ እያለ በ፶ ዎቹ ዓ.ም. ለቆሮንጦስ ሰዎች የጻፈው የመጀመሪያ መልዕክት ነው ። ፲፮ ምዕራፎች ይይዛል ። ይህ ፪ኛ ምዕራፍ ሲሆን በ፲፮ ንዑስ ክፍሎች ይከፈላል ።


ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንጦስ ሰዎች መልዕክት የጻፈበት ምክኒያት ብዙ ሲሆን ከብዙዎች በጥቂቱ ፣ ከመምህሮቻቸው መዐረግ ሳይደርሱ ደረስን እያሉ በብዙ ቐንቐ በሚናገሩ መምህሮቻቸው እንደነ ራሱ ፣ ጳውሎስ ፣ አጵሎስ... ላይ የሚታበዩ ስለተነሱ ለነዚህ እንደ ዘለፋ እንዲሆን ፤ በቆሮንቶስ ምዕመናን መሀከል መከፋፈላቸውን ሰምቶ ከዚህ ስህታቸው እንዲታረሙ ፤ በተጨማሪም ዓለምን ለማሳፈር እግዚአብሔር ታላቁን ሚሥጥር በዓለም በተናቁት ሰዎች እንዲገለፅ ማድረጉን ለማሳወቅ ጻፈው ።

የሐዋርያው ጳውሎስ መልዕክት ፩ኛ ወደ ቆሮንጦስ ምዕራፍ ፪

1፤እኔም፥ወንድሞች፡ሆይ፥ወደ፡እናንተ፡በመጣኹ፡ጊዜ፡በቃልና፡በጥበብ፡ብልጫ፡ለእግዚአብሔር፡ ምስክርነቴን፡ለእናንተ፡እየነገርኹ፡አልመጣኹም። 2፤በመካከላችኹ፡ሳለኹ፡ከኢየሱስ፡ክርስቶስ፡በቀር፥ርሱም፡አንደ፡ተሰቀለ፡ሌላ፡ነገር፡እንዳላውቅ፡ቈርጬ፡ ነበርና። 3፤እኔም፡በድካምና፡በፍርሀት፡በብዙ፡መንቀጥቀጥም፡በእናንተ፡ዘንድ፡ነበርኹ፤ 4-5፤እምነታችኹም፡በእግዚአብሔር፡ኀይል፡እንጂ፡በሰው፡ጥበብ፡እንዳይኾን፥ቃሌም፡ስብከቴም፡መንፈስንና፡ ኀይልን፡በመግለጥ፡ነበረ፡እንጂ፥በሚያባብል፡በጥበብ፡ቃል፡አልነበረም። 6፤በበሰሉት፡መካከል፡ግን፡ጥበብን፡እንናገራለን፥ነገር፡ግን፥የዚችን፡ዓለም፡ጥበብ፡አይደለም፡ የሚሻሩትንም፡የዚችን፡ዓለም፡ገዢዎች፡ጥበብ፡አይደለም፤ 7፤ነገር፡ግን፥እግዚአብሔር፡አስቀድሞ፡ከዘመናት፡በፊት፡ለክብራችን፡የወሰነውን፥ተሰውሮም፡የነበረውን፡ የእግዚአብሔርን፡ጥበብ፡በምስጢር፡እንናገራለን፥ 8፤ከዚችም፡ዓለም፡ገዢዎች፡አንዱ፡እንኳ፡ይህን፡ጥበብ፡አላወቀም፤ዐውቀውስ፡ቢኾኑ፡የክብርን፡ጌታ፡ ባልሰቀሉትም፡ነበር፤ 9፤ነገር፡ግን፦ዐይን፡ያላየችው፡ዦሮም፡ያልሰማው፡በሰውም፡ልብ፡ያልታሰበው፡እግዚአብሔር፡ለሚወዱት፡ ያዘጋጀው፡ተብሎ፡አንደ፡ተጻፈ፥እንዲህ፡እንናገራለን። 10፤መንፈስም፡የእግዚአብሔርን፡ጥልቅ፡ነገር፡ስንኳ፡ሳይቀር፡ዅሉን፡ይመረምራልና፥ለእኛ፡እግዚአብሔር፡ በመንፈሱ፡በኩል፡ገለጠው።

ቁጥር ፲፩ - ፲፮

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

11፤በርሱ፡ውስጥ፡ካለው፡ከሰው፡መንፈስ፡በቀር፡ለሰው፡ያለውን፡የሚያውቅ፡ሰው፡ማን፡ነው፧እንዲሁም፡ ደግሞ፡ከእግዚአብሔር፡መንፈስ፡በቀር፡ለእግዚአብሔር፡ያለውን፡ማንም፡አያውቅም። 12፤እኛ፡ግን፡ከእግዚአብሔር፡እንዲያው፡የተሰጠንን፡እናውቅ፡ዘንድ፡ከእግዚአብሔር፡የኾነውን፡መንፈስ፡ እንጂ፡የዓለምን፡መንፈስ፡አልተቀበልንም። 13፤መንፈሳዊውን፡ነገር፡ከመንፈሳዊው፡ነገር፡ጋራ፡አስተያይተን፡መንፈስ፡በሚያስተምረን፡ቃል፡ይህን፡ ደግሞ፡እንናገራለን፡እንጂ፡የሰው፡ጥበብ፡በሚያስተምረን፡ቃል፡አይደለም። 14፤ለፍጥረታዊ፡ሰው፡የእግዚአብሔር፡መንፈስ፡ነገር፡ሞኝነት፡ነውና፥አይቀበለውም፤በመንፈስም፡ የሚመረመር፡ስለ፡ኾነ፡ሊያውቀው፡አይችልም። 15፤መንፈሳዊ፡ሰው፡ግን፡ዅሉን፡ይመረምራል፡ራሱ፡ግን፡በማንም፡አይመረመርም። 16፤እንዲያስተምረው፡የጌታን፡ልብ፡ማን፡ዐውቆት፡ነው፧እኛ፡ግን፡የክርስቶስ፡ልብ፡አለን።