1991
Appearance
ክፍለ ዘመናት፦ | 19ኛ ምዕተ ዓመት - 20ኛ ምዕተ ዓመት - 21ኛ ምዕተ ዓመት |
አሥርታት፦ | 1960ዎቹ 1970ዎቹ 1980ዎቹ - 1990ዎቹ - 2000ዎቹ 2010ሮቹ 2020ዎቹ
|
ዓመታት፦ | 1988 1989 1990 - 1991 - 1992 1993 1994 |
1991 አመተ ምኅረት
- ጥቅምት ፳ - «ሃሪኬን ሚች» የተባለው ታላቅ አውሎ ነፋስ ባስከተለው የጭቃ ጎርፍ ኒካራጓ ላይ በጥቂቱ ሁለት ሺህ ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ።
- ኅዳር ፬ - የአሜሪካው ፕሬዚደንት ቢል ክሊንተን በአመንዝረኛነት ፖላ ጆንስ በተባለች ሴት ተከሰው ለአራት ዓመታት ከተከራከሩ በኋላ ጥፋተኛነታቸውን ሳያምኑ ስምንት መቶ ኃምሳ ሺህ [[የአሜሪካ ዶላር] በመክፈል ክርክሩን አዘጉ።
- ኅዳር ፲ - በአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የሕግ ሸንጎ በሞኒካ ሌዊንስኪ የአመንዝራ ኃጢአት በፈጸሙት በፕሬዚደንት ክሊንተን ላይ የክሱ ዝርዝር እና ምስክሮች መሰማት ጀመረ።
- ኅዳር ፳፯ - በቬኔዙዌላ አገር ወታደራዊው መኮንን ሁጎ ሻቬዝ ፍሪያስ በፕሬዚደንትነት ተመረጠ።
- የካቲት ፳፩ - የኢትዮጵያ ሠራዊት በኤርትራ ወራሪ ሠራዊት ላይ የባድመ ድል ተቀዳጀ።
- ሚያዝያ ፩ - የኒጄር ፕሬዚደንት ኢብራሂም ባሬ ማይናሳራ በአገሪቱ በተካሄደው ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ተገደሉ።
- ሐምሌ ፱ - የሟቹ የፕሬዚደንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ ልጅ ጆን ኤፍ ኬኔዲ ጁንየር ከሚስቱ እና ከሚስቱ እህት ጋር በበረራ ላይ እንዳሉ በአውሮፕላን አደጋ አትላንቲክ ውቅያኖስ ውስጥ በመስመጥ ሕይወታቸውን አጡ።
- ሐምሌ ፲፮ - የሞሮኮው ንጉሥ ዳግማዊ ሀሰን ሲሞቱ ንጉሥ ሞሐመድ አራተኛ ተብለው የንጉሥነት ዘውድ ጭነው ነገሡ።
- ነሐሴ ፭ - በአውሮፓ እና በእስያ አኅጉራት ያሉት በአውሮፓውያን አቆጣጠር የምዕተ ዓመቱን የመጨረሻ ድፍን የፀሐይ ግርዶሽ ተመልክተዋል።