ሐምሌ ፱
Appearance
ሐምሌ ፱ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፱ ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ሉቃስ ፶፮ ቀናት በዘመነ ዮሐንስ፤ በዘመነ ማቴዎስ፤ እና በዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፶፭ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፯፻፹፪ ዓ/ም- ዲስትሪክት ኦፍ ኮሉምቢያ (District of Columbia) የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት መቀመጫ ዋና ከተማ ሆነ።
- ፲፱፻፳፫ ዓ/ም - ዓፄ ኃይለ ሥላሴ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ሆነው ዘውድ በጫኑ በዘጠነኛው ወር የሀገሪቱን የመጀመሪያውን ሕገ መንግሥት በንጉሠ ነገሥቱ፣ አልጋ ወራሹ፣ ጳጳሳቱ፣ መሳፍንቱ፣ ሚኒስትሮቹ እና ባላባቶቹ መኳንንቱም ፈርመውበት በዐዋጅ ተግባር ላይ ዋለ።
- ፲፱፻፴፯ ዓ/ም - ዩናይትድ ስቴትስ የመጀመሪያውን የሙከራ አቶሚክ ቦንብ አፈነዳ።
- ፲፱፻፷፩ ዓ/ም - ጨረቃ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰውን ልጅ ይዞ ያረፈው አፖሎ 11 መንኮራኩር ከኬኔዲ የጠረፍ ማዕከል ተተኮሰ።
- ፲፱፻፺፩ ዓ/ም - የሟቹ የፕሬዚደንት ኬኔዲ ልጅ ጆን ኤፍ ኬኔዲ ጁንየር ከሚስቱ እና ከሚስቱ እህት ጋር በበረራ ላይ እንዳሉ በአውሮፕላን አደጋ አትላንቲክ ውቅያኖስ ውስጥ በመስመጥ ሕይወታቸውን አጡ።
- ፲፱፻፺፩ ዓ/ም - የሟቹ የፕሬዚደንት ኬኔዲ ልጅ ጆን ኤፍ ኬኔዲ ጁንየር
- (እንግሊዝኛ) http://en.wikipedia.org/wiki/July 16
- ‘ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ’ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ፣ ፩ኛ መጽሐፍ፣ ፲፱፻፳፱ ዓ/ም
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |