Jump to content
አማርኛ ውክፔድያን አሁኑኑ ማዘጋጀት ትችላላችሁ - ተሳተፉበት!

ኡቱ-ኸጛል

ከውክፔዲያ
የ23:49, 26 ፌብሩዌሪ 2014 ዕትም (ከCodex Sinaiticus (ውይይት | አስተዋጽኦ) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)

ኡቱ-ኸጛልኡሩክና የሱመር ንጉሥ ነበር። በ1985 ዓክልበ. ግድም የጉታውያንን መጨረሻ ንጉሥ ቲሪጋንን ማረከና ጉታውያንን ከሱመር አስወጣቸው። ስለዚህ ኡሩክ የሱመር ላዕላይነት ያዘ። በሱመራዊ ነገሥታት ዝርዝር በአብዛኛው ቅጂ 427 ዓመታት እንደ ገዛ ሲል ሌሎች ቂጂዎች 27 ዓመታት ወይም 7 ዓመታት ይላሉ። ሆኖም ከኡቱ-ኸጛል የዓመት ስሞች አንድ ብቻ ይታወቃል፣ እሱም «ኡቱ-ኸጛል ንጉሥ የሆነበት ዓመት» ይባላል። ስለዚህ ከአንድ አመት በላይ ብዙ እንደ ቀረ አጠያያቂ ነው። ከኡር አለቃ ኡር-ናሙና ከላጋሽ አለቃ ናማሐኒ መካከል አንድ ጸብ ተነሥቶ ኡቱ-ኸጛል ክርክሩን ለላጋሽ አደለ። በቅርብ ጊዜ ውስጥ ግን ኡር-ናሙ የሱመር ላዕላይ ንጉሥ ሆነ። በአንድ ሰነድ ዘንድ ኡቱ-ኸጛል አንዱን መስኖ ገደብ በመመርመር እያለ በወንዙ ወድቆ ሰመጠ። በዋይድነር ዜና መዋዕል በተባለ ጽላት ኡቱኸጛል «የተቀደሠውን ከተማ» ባቢሎንን ስለ ወነጀለ የጠፋ ነው።

ቀዳሚው
ቲሪጋን
ሱመር ነጉሥ
1985-1984 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ኡር-ናሙ