ሰመንካሬ ነብኑኒ
Appearance
==
ሰመንካሬ ነብኑኒ | |
---|---|
የግብጽ ፈርዖን | |
ግዛት | 1800-1798 ዓክልበ. ግ. |
ቀዳሚ | 6 አመነምሃት |
ተከታይ | ሰኸተፒብሬ |
ሥርወ-መንግሥት | 13ኛው ሥርወ መንግሥት |
==
ሰመንካሬ ነብኑኒ (ወይም ነብኑን፣ ነብነኑ) ላይኛ ግብጽ በ2ኛው ጨለማ ዘመን (13ኛው ሥርወ መንግሥት) ከ1800 እስከ 1798 ዓክልበ. ግድም ድረስ የገዛ ፈርዖን ነበረ። የ6 አመነምሃት ተከታይ ነበረ።
ሕልውናው ከአንድ ጽላት ብቻ ተረጋግጧል። ይህም ጽላት በሲና ልሳነ ምድር በኩልና እርሳስ ማዕድን ቦታ ተገኘ። በኋላ ዘመን በተጻፈው በቶሪኖ ቀኖና ነገሥታት ዝርዝር ላይ ሲጠቀስ የዘመኑ ርዝመት ግን በከፊል ከሰነዱ ጠፍቶ ስለ ሆነ፣ «ነብኑኒ <..> እና ፳፪ ቀን ገዛ» ብቻ ሊነብ ይቻላል። የግብጽ ታሪክ ሊቅ ኪም ራይሆልት ለ፪ ዓመታት ብቻ ያሕል እንደ ነገሠ የሚል ግመት አቅርቧል። በራይሆልት አሳብ ተከታዩ ሰኸተፒብሬ ነበረ።
ቀዳሚው 6 አመነምሃት |
የግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን | ተከታይ ሰኸተፒብሬ |
- K.S.B. Ryholt: The Political Situation in Egypt during the Second Intermediate Period, c. 1800 – 1550 BC, Carsten Niebuhr Institute Publications, vol. 20. Copenhagen: Museum Tusculanum Press, 1997 (እንግሊዝኛ)