Jump to content

ፎጣድ ካይርፕተቅ እና ፎጣድ አይርግጠቅ

ከውክፔዲያ
የ00:50, 25 ኦገስት 2015 ዕትም (ከCodex Sinaiticus (ውይይት | አስተዋጽኦ) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)

ፎጣድ ካይርፕተቅ እና ፎጣድ አይርግጠቅ279 እስከ 280 ዓም ድረስ የአየርላንድ ጋርዮሽ ከፍተኛ ነገሥታት ነበሩ። ሁለቱ ፎጣዶች ደግሞ ወንድሞች ነበሩ።

በአይርላንድ ታሪኮች ዘንድ ቀዳሚያቸው ካይርብሬ ሊፌቃይር ከተገደለ በኋላ፣ ለአንድ አመት ከፍተኛ ንጉሥነቱን በጋራ ያዙ፤ ከዚያ ግን ፎጣድ አይርግጠቅ ወንድሙን ገደለ እና ካይልቴ ማክ ሮናይን አይርግጠቅን ገደለው። ከዚያ ፍያቃ ስሮይፕቲኔ ከፍተኛ ንጉሥ ሆነ።

የቲገርናቅ ዜና መዋዕል (1080 ዓም ተቀነባብሮ) ፎጣዶቹን አይጠቅስም። የካይርብሬ ዘመን በ253 ዓም እንደ ጀመረ፣ ለ25 ዓመታት እንደ ቆየ ይዘግባል። (ሌሎቹ ምንጮች ካይርብሬን 26 ዓመታት ይሰጡታል)። የፍያቃም ዘመን በ280 እንደ ጀመረ ሲለን በዚህ አቆጣጠር የፎጣዶች ዓመት 279-280 ዓም መሆን አለበት።