Jump to content

ጦርነት

ከውክፔዲያ
የ01:14, 23 ጃንዩዌሪ 2018 ዕትም (ከTil Eulenspiegel (ውይይት | አስተዋጽኦ) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)

ጦርነት ግዛቶች ወይም ኅብረተሠቦች በመሣሪያዎች ሲታገሉ ነው። በጦርነት ጊዜ ሥራዊቶቹ ብዙ ግፍና መግደል ሊያድርጉ ይቻላል። በጥንታዊ ግብጽ ጥንታዊ መንግሥት 3125-2763 ዓክልበ. ግድም የሔሩ ወገን (የፈርዖኖች ወገን) ብዙ ጊዜ ጦርነት በአካባቢያቸው ሕዝቦች እንዳደረጉ ይታወቃል። በኋላ በመስጴጦምያ ታሪክ ኤላምኪሽ የተባሉት ጥንታዊ አገራት እርስ በርስ ጦርነት ጀመሩ (2384 ዓክልበ.)። በትንሽ ጊዜ ላይ ጦርነቶች በቻይና፣ በአፍሪቃና በአውሮፓ በየትም ተከሰቱ። ከዚያ ወዲህ ምንጊዜም በዓለም ላይ አንዳንድ ጦርነቶች በአንዳንድ አገራት ሊገኙ ይቻላል፤ በአንድም አገር ጦርነት በማይገኝበት ጊዜ ወይም ከተጨረሰ በኋላ ሰላም ይባላል።

የመንግሥታት ማህበርና ቀጥሎ የተባበሩት መንግሥታት የአለም አገራት ሰላም እንዲጠብቅ ሠርተዋል፣ ሆኖም በአንዳንድ ቦታ ጦርነት እስካሁን ድረስ ይከሠታል።