2 እሽመ-ዳጋን በአሦር ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ ለ16 ዓመታት (ከ1555 እስከ 1539 ዓክልበ. ገደማ) የአሦር ንጉሥ ነበረ።
የቀዳሚው የ2 ሻምሺ-አዳድ ልጅ ይባላል። ተከታዩ 3 ሻምሺ-አዳድ ግን የሌላ እሽመ-ዳጋን (የሹ-ኒኑዓ ልጅ የሆነ) ልጅ እንደ ነበር ይላል። ከዚህ ዘመን ምንም ሥነ ቅርስ ወይም ሌላ መረጃ የለንም።