Jump to content

ክርስቶስ

ከውክፔዲያ
የ17:44, 25 ኖቬምበር 2018 ዕትም (ከ81.234.233.22 (ውይይት) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)

ክርስቶስ ማለት ከግሪክኛ ቋንቋ Χριστός ነው፤ ይህም ለመሢሕ (ከዕብራይስጥ ማሺያሕ ወይም «የተቀባ») ትርጒም ነው። በክርስትና እምነት እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ (ረቢ ይሆሹዓ) ስያሜ ይጠቀማል፤ «የተቀባ» ማለትም ወልድ (ከሥላሴ አንዱ) ሆኖ ለንጉሥነት ማለት ነው። «በእርሱ የመለከት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና» (ቈላስ. ፪፣፱) በአዲስ ኪዳን የተመሠረተ እምነት ነው። በትምህርተ ሥላሴ ዘንድ እሱ ብቻ መላው አምላክ ሳይሆን የፈጣሪው ክንድ ወይም አካል ነው፤ እንደ አብመንፈስ ቅዱስ ሆኖ ደግሞ በሌሎች ቦታዎች አለ።

ብሉይ ኪዳን ደግሞ “መሲሕ” مسيح የሚለው የአረቢኛ ቃል “መሢሐ” מָשִׁ֫יחַ የሚለው የእብራይስጥ ቃል “መሢሕ” ክמשיחא የሚለው የአረማይ ቃል ሴማዊ መነሻ ሲኖረው ትርጉሙ “የተቀባ” ማለት ነው፣ በግሪክ ደግሞ “ክርስቶስ” Χριστός ነው፤ ይህ ማእረግ በብሉይ ኪዳን ለተለያየ ነገስታትና ነቢያት በግሪኩ ሰፕቱጀንት ላይ “ክርስቶስ” Χριστός በእብራይስጡ ደግሞ መሢሐ” מָשִׁ֫יחַ ተብሎ አገልግሎት ላይ ውሏል፤ መቀባት መሾምን ያመለክታል በአምላክ የተቀቡ የአምላክ መሢሖች ብዙ ናቸው፦ 1ኛ ዜና 16፥22 “መሢሖቼን” בִּמְשִׁיחָ֔י አትዳስሱ፥ “በነቢያቴም” ክፉ አታድርጉ ብሎ፥ ሰው ግፍ ያደርግባቸው ዘንድ አልፈቀደም ስለ እነርሱም ነገሥታትን ገሠጸ። መዝሙረ ዳዊት 105፥14-15 “መሢሖቼን” בִּמְשִׁיחָ֔י አትዳስሱ፥ “በነቢያቴም” ክፉ አታድርጉ ብሎ፥ ሰው ግፍ ያደርግባቸው ዘንድ አልፈቀደም ስለ እነርሱም ነገሥታትን ገሠጸ።

አንደኛ “ሳኦል” 1ሳኦል በትንቢት የተነገረለት መሢሐዊ ንጉስ ነው፦ 1 ሳሙ 2:10 እግዚአብሔር እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል፤ “ለንጉሡም” ኃይል ይሰጣል፤ “የመሲሑንም” מְשִׁיחֽוֹ ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል።

ይህንን ጥቅስ የአይሁድ ምሁራን እና ለዘብተኛ የብሉይ ተንታኞች ለሳኦል እንደሆነ ያትታሉ፤ በተጨማሪም በሳሙኤል ዘመን የተቀባ መሢሕ ሳኦል እንደሆነ በቁና መረጃ አለ፦ 1ሳሙ 10:1፤ ሳሙኤልም የዘይቱን ብርሌ ወስዶ በራሱ ላይ አፈሰሰው፥ ሳመውም፥ እንዲህም አለው። በርስቱ ላይ አለቃ ትሆን ዘንድ እግዚአብሔር “ቀብቶሃል” מְשָׁחֲךָ ֧፤ 1ሳሙ 12፥3 እነሆኝ በእግዚአብሔርና “በመሲሑ” מְשִׁיח֗וֹ ፊት መስክሩብኝ የማንን በሬ ወሰድሁ? 1ሳሙ 12፥5 እርሱም፦ በእጄ ምንም እንዳላገኛችሁ እግዚአብሔርና “መሲሑ” מְשִׁיח֗וֹ ዛሬ በእናንተ ላይ ምስክሮች ናቸው አላቸው፤

ሁለተኛ “ዳዊት” 2 ሳሙ 22፥51 የንጉሡን መድኃኒት ታላቅ ያደርጋል፤ ቸርነቱንም ለመሲሑ לִמְשִׁיח֛וֹ ለዳዊትና ለዘሩ፥ ለዘላለም ይሰጣል። 2 ሳሙ 23፥1 የዳዊትም የመጨረሻ ቃሉ ይህ ነው። ከፍ ከፍ የተደረገው፥ የያዕቆብም አምላክ መሢሕ מְשִׁ֙יחַ֙፥ በእስራኤል ዘንድ መልካም ባለ ቅኔ የሆነ፥ የእሴይ ልጅ የዳዊት ንግግር፤ መዝ 132:17 በዚያ ለዳዊት ቀንድን አበቅላለሁ፥ “ለመሢሔ” לִמְשִׁיחִֽי ሰው መብራትን አዘጋጃለሁ።

ሶስተኛ “ሰለሞን” 1ሳሙ 2:35 የታመነም ካህን ለእኔ አስነሣለሁ፥ በልቤም በነፍሴም እንዳለ እንዲሁ ያደርጋል፤ እኔም የታመነ ቤት እሠራለታለሁ፥ ዘመኑን ሁሉ በመሢሔ מְשִׁיחִ֖י ሰው ፊት ይሄዳል።

ይህ ጥቅስ ትንቢት ሲሆን ትንቢቱም ስለ ካህንና ካህኑ የሚሄድበት መሢሑ ናቸው፤ ምሁራን ካህኑ ሳዶቅ ሲሆን መሢሑ ደግሞ ቤት የሰራው ሰለሞን ነው፦ 1 ኛ ነገሥት 1፥39 ካህኑም ሳዶቅ ከድንኳኑ የቅብዓቱን ቀንድ ወስዶ ሰሎሞንን ቀባ וַיִּמְשַׁ֖ח፤ ቀንደ መለከትም ነፉ፤ ሕዝቡም ሁሉ፦ ሰሎሞን ሺህ ዓመት ይንገሥ አሉ።

አራተኛ “ሴዴቂያስ” ምሁራን በባቢሎን ምርኮ ጊዜ በጉድጓድ የተያዘው ሴዴቅያስ እንደሆነ ያትታሉ፤ ይህም ንጉስ መሲህ ተብሏል፦ ሰቆእንኖራለንቃው ኤርምያስ 4፥20 ሬስ። ስለ እርሱ። በአሕዛብ መካከል በጥላው በሕይወት ያልነው “የእግዚአብሔር መሢሕ” מְשִׁ֣יחַ፥ የሕይወታችን እስትንፋስ፥ በጕድጓዳቸው ተያዘ።

አምስተኛ “ሙሴና ኤልያስ” ዘካ 4:14 እርሱም። በምድር ሁሉ ጌታ አጠገብ የቆሙት “ሁለቱ የተቀቡት” הַיִּצְהָ֑ר እነዚህ ናቸው አለኝ።

በምድር ሁሉ ጌታ አጠገብ የቆሙት “ሁለቱ የተቀቡትየተባሉት ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማይን ካዘጋው ከኤልያስና ውኃዎችንም ወደ ደም ካስለወጠው ከሙሴ ሌላ እነማን ሊሆኑ ይችላሉ? ምሁራን በዚህ ሸክ የላቸውም፦ ራእይ 11፥3-10 “ለሁለቱም ምስክሮቼ” ማቅ ለብሰው ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን “ትንቢት” ሊናገሩ እሰጣለሁ። እነዚህ “በምድር ጌታ ፊት የሚቆሙ” ሁለቱ ወይራዎችና ሁለቱ መቅረዞች ናቸው። ዘካርያስ 4፥11 እኔም መልሼ፦ በመቅረዙ በስተ ቀኝና በስተ ግራ ያሉ እነዚህ “ሁለት የወይራ ዛፎች” ምንድር ናቸው? አልሁት። ዘካ 4:14 እርሱም። በምድር ሁሉ ጌታ አጠገብ የቆሙት “ሁለቱ የተቀቡት” הַיִּצְהָ֑ר እነዚህ ናቸው አለኝ።

ስድስተኛ “ኢየሱስ” መዝሙረ ዳዊት 2፥2 የምድር ነገሥታት ተነሡ፥ አለቆችም በእግዚአብሔርና በመሢሑ מְשִׁיחֽוֹ ላይ እንዲህ ሲሉ ተማከሩ።

ክርስቶስ ቅድመ ዓለም ያለ እናት ከባሕርይ አባቱ ከአብ ፣ ድኀረ ዓለም ያለ አባት ከቅድስት ድንግል ማርያም በሥጋ የተወለደ፣ ሥጋን እና ነፍስን ከቅድስት ድንግል ማርያም ነሥቶ ሰው የሆነ የባሕርይ አምላክ ነው::የሰውን ልጅ ከባርነት ነጻ ለማውጣት ፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከባርነት ወደ ነጻነት፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን ለማሸጋገር፤ ፍቅር ከዙፋኑ ስቦት የወረደ፤ አምላክ ነው ኢየሱስ ክርስቶስ::

ክርስቶስ ኢየሱስ ቸር እረኛ፣ አምላክ፣ ወልደ አምላክ፣ ሰውም አምላክም፣ ሲሆን በክርስቲያኖች መካከል ስለ ባሕርይው የተለያዩ አመለካከቶች አሉ::በጥንታዊት ቤተክርስቲያን ማለትም ከጉባኤ ኬልቄዶን በፊት አንዲት ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን በነበረችበት ወቅት ያለው አስተምህሮ 'ክርስቶስ እግዚአብሔር ነው ፤አምላክ ነው፤ አምላክ ደግሞ አንድ ባሕርይ አለው፤ ክርስቶስም አንድ ባህርይ አንድ አካል አለው ይል ነበር:: ከሁለት አካል አንድ አካል፣ ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ ፣ ሰውም አምላክም፣ ትስእብት(ሥጋ) ከመለኮት ጋር ፍጹም ከተዋሐደ በኋላ እንደ ሁለት አካል ወይም ባህርይ አይቆጠርም ፤ብላ ታስተምር የነበረች አለማቀፋዊት ቤተክርስቲያን በጉባዔ ኬልቄዶን ከሁለት ተከፈለች::ይህም አንድ ባሕርይ እና ሁለት ባሕርይ በማለት ነበር::

ነገር ግን ማንም ክርስቲያን ቢሆን አሁን ላይ ያለው እምነት ክርስቶስ የዓለም መድህን፣ የእግዚአብሔር ልጅ ፣ የሕይወት መገኛ፣ ህብስተ ሕይወት፣ መንገድ እና መልካም እረኛ እንደሆነ፤ የሰውን ልጅ ድንቅ በሆነ ፍቅሩ ከሰይጣን አገዛዝ ነጻ ያወጣ ፣ በምድር አባት በሰማይ እናት የሌለው ፣ ሁለት ልደታት ያለው፣ ከብርሃን የተገኘ የዓለም ብርሃን ፣ ቅን ፈራጅ እና እውነተኛ ዳኛ እንደሆነ ይታመናል:: ክርስቶስ በክርስትና ዓለም ላሉ ሰወች መራራ ሞትን ሞቶ ሕይወትን የሰጠ ፣መራራ ከርቤን ጠጥቶ ጣፋጭ ወይንን(ደሙን) ያጠጣ፣ ራቁትን ሆኖ ፀጋን ያለበሰ፣ ተሰቅሎ ሰይጣንን ከፊታችን ጠርቆ ያስወገደ ፣ ተርቦ ሰማያዊ ሕብስትን ያበላ የሁሉም አዳኝ መሆኑ ይታመናል::

ክርስቶስ-«ሁሉም በእርሱ ሆነ፥ (በእርሱ ተፈጠረ)፥ ከሆነውም (ከተፈጠረውም) ሁሉ ያለ እርሱ ምንም የሆነ የለም። ዮሐ ፩፥፫።-ተብሎ እንደተጻፈ፤ ደግሞም በትንቢት ነብዩ ኢሳይያስ <<ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።>> ተብሎ እንደተተነበየ፤ በወንጌልም <<ቃል እግዚአብሔር ነበረ>> ተብሎ የምሥራች እንደተነገር፤ በዮሐንስ ወንጌል ሐዋርያው ቶማስ ጌታዬ አምላኬ ብሎ እንደመሰከረ፤ ክርስቶስ እግዚአብሔር መሆኑ በብዛት ባለንበት ዓለም ይታመናል::ነገር ግን ከዚህ የተለየ እምነት በአለማችን እንዳለም ይታወቃል::

: