Jump to content

እብናት (ወረዳ)

ከውክፔዲያ
የ13:05, 25 ኦክቶበር 2022 ዕትም (ከEN-Jungwon (ውይይት | አስተዋጽኦ) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)

እብናት ከ1950ዎቹ ጀመሮ በወረዳነት የተዋቀረ፣ በደቡብ ጎንደር የሚገኝ ክፍል ሲሆን የአስተዳደር ማዕከሉ በተመሳሳይ ስም እብናት ከተማ ነው።[1] እብናት ወረዳ ውስጥ 35 የገጠር ቀበሌዎች እና 1 የከተማ ቀበሌ ይገኛል።

ጥር 12፣ 1600 ዓ.ም. ዓፄ ሱሰንዮስ ወደዚህ አካባቢ በዘመተ የኦሮሞ ቡድን ላይ ድንገት ጦርነት በመክፈት ወደ 12፣000 የቡድኑ አባሎችን በመግደል እና በራሱ ላይ ደግሞ 400 ጉዳት በማድረስ በታሪክ ተጠቅሶ ይገኛል። [2] ምንም እንኳ በግል እና በአካባቢያዊ ጥቅም ምክንያት መጀመሪያ ላይ የአርበኞች ትግል እብናት ውስጥ የቀዘቀዘ የነበር ቢሆንም በኋላ ግን የበጌምድር የአርበኞች ትግል ማዕከል በመሆን በጣሊያን ወራሪ ሃይል ላይ ብዙ ትግል በዚህ ቦታ ተካሂዷል[3]። በ1974 ዓ.ም. እብናት ውስጥ የርሃብተኞች መርጃ ካምፕ የተቋቋመ ሲሆን፣ ካምፑ በመጀመሪያ 7፣000 ሰዎችን ሲያስተናግድ በ1977 ዓ.ም እስከ 50፣000 ሰዎችን አስጠልሎ ነበር። በ'77 ዓ.ም. በደርግ ባለስልጣን ትዕዛዝ ካምፑ ፈርሶ ሰዎቹ ያልምንም ርህራሄ ወደ መጡበት ወሎ ክፍለሃገር እንዲሄዱ የታዘዙ ሲሆን፣ በተባበሩት መንግስታት ሰራተኞች ጣልቃ ገብነት፣ ከካምፑ ተሰደው ከተደበቁበት ያካባቢው ተራራ እንደገና ተመልሰው በዚሁ ካምፕ ኑሮ እንደጀመሩ የተባበሩት መንግስታት ሰነዶች ያስታውቃሉ[4]። አወ እብናት ታሪካዊ ቦታናት

የሕዝብ ስብጥር

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
የእብናት ወረዳ ሕዝብ ስብጥር
ዓ.ም.** የሕዝብ ብዛት
1986
163,413
1999
220,177


እብናት
ከምከም ሰሜን ጎንደር ~  км. ዋግ ሒምራ
ከምከም
~  км.
እብናት
እብናት
ሰሜን ወሎ ~  км.
ፎገራ ~  км. ፋርጣ ~  км. ላይ ጋይንት
  1. ^ "Local History in Ethiopia" Archived ሜይ 28, 2011 at the Wayback Machine The Nordic Africa Institute website (accessed 6 November 2007)
  2. ^ James Bruce, Travels to Discover the Source of the Nile (1805 edition), vol. 3, pp. 295f
  3. ^ "Archive copy". Archived from the original on 2012-05-10. በ2012-08-27 የተወሰደ.
  4. ^ "Archive copy". Archived from the original on 2012-05-10. በ2012-08-27 የተወሰደ.

{{|12|10|N|38|05|E|display=title|type:adm3rd_region:ET}}