Jump to content

መርካቶ

ከውክፔዲያ
መርካቶ

መርካቶ ገበያ ወይም አዲስ መርካቶ (ከጣልያንኛው ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙ ደግሞ ገበያ ማለት ነው።) በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ ውስጥ በዋነኛነት አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ እና በአጎራባች አከባቢዎች የተካለለ ሠፊ ገበያ ነው። መርካቶ በአፍሪካ ሠፊው ገላጣ ገበያም ነው። በዚህም በብዙ ካሬ ኪሎሜትር በሚቆጠር መሬት ላይ ከ13,000 በላይ ሠዎችን በ7,100 የሚደርሡ የንግድ ሠቆች ውስጥ የያዘ እንደሆነ ይገመታል።

በዚህ ገበያ ውስጥ በአብዛሃኛው ጊዜ የሚዘወተሩት በተለምዶ ሀገር በቀል የሆኑ የጥራጥሬ ምግቦች እና ፍራፍሬዎች እንዲሁም በዋነኛነት ቡና ናቸው። ይህ ገበያ የተዋቀረው በዘረኛ የጣልያን ገዥዎች ፖሊሲ ሲሆን ያደረጉትም ታሪካዊውን የቅዱስ ጊዮርጊስ መርካቶ ለጣልያናዊያን ብቻ በመከለል ዋናዎቹን የአረብ ነጋዴዎች ወደ መዕራብ ከግማሽ ማይል በላይ ርቀው እንዲነግዱ በማስገደድ ነበር። ቀስ በቀስ እነዚህን የአረብ ነጋዴዎች የሀገሪቱ ተወላጅ በሆኑ ነጋዴዎች በመተካት ከእ.አ.አ. 1960 ጀምሮ ሀገርኛ ቃና ያለው ገበያ ሊሆን ችሏል። የአዲስ አበባ መርካቶ በሺዎች የሚቆጠሩ ሡቆች እና ትልልቅ የገበያ አዳራሾች (በውስጡም እያንዳንዱ ከሠባ በላይ ሡቆችን የያዙን) ይዟል። «ተራ»:–በመርካቶ ውስጥ "ተራ" በመባል የሚታወቁ ራሳቸውን የቻሉ የመርካቶ ክፍሎች አሉ።ለምሳሌ ያህል:– ምናለሽ ተራ ቆርቆሮ ተራ ጋዝ ተራ ዶሮ ተራ ቦንብ ተራ አውቶቢስ ተራ ጭድ ተራ ጫት ተራ ቆጮ ተራ ብረት ተራ ቡና ተራ ሶማሌ ተራ ሳጥን፣ጠረጴዛ፣ሸክላ፣ፎዴ፣ሚሊቴሪ፣ድር፣ሚስማር፣ሸማ፣ሸራ፣ወራባተራ ወዘተ… መርካቶ ከአብነት በተለይም ከሞላማሩ ጀምሮ እስከ ፒያሳ…በጎን ደግሞ ተመሳሳዩን ያህል ትልቅ ስፋት የያዘ ከአፍሪካ አንደኛ የሆነ የገበያ ዓለም ነው። በዚህ ቦታ ውስጥ የማይዘነጉት የአንዋር መስጂድ እና የራጉኤል ቤተክርስቲያን ይገኛሉ።


  • Zewde, Bahru. (1991) A History of Modern Ethiopia. London: James Currey.
  • Bonsor, Sacha. (2005) "Merkato Mania Archived ጁላይ 13, 2011 at the Wayback Machine" Impressions Magazine. British Airways. (accessed March 8, 2006)