Jump to content

ሙሴዎን

ከውክፔዲያ
የእስክንድርያ መጻሕፍት ቤት

ሙሴዎንእስክንድርያግብጽ በግሪኮች ፈርዖን ፩ በጥሊሞስ የተመሠረተ ጥንታዊ የከፍተኛ ትምህርት ቤት ተቋም ነበር። ምናልባት ከ300 ዓክልበ. ግድም እስከ 264 ዓም. ድረስ ቆየ።

ዝነኛው የእስክንድርያ መጻሕፍት ቤት በዚህ ውስጥ ተገኘ። መጻሕፍት በማንኛውም ቋንቋ ከግሪክ አገርይሁዳመስጴጦምያፋርስሕንድ ወዘተ. ተከማችተው ተተረጎሙ።

በተቋሙ ውስጥ ከተማሩት ጥናቶች መካከል በተለይ ሙዚቃቅኔፍልስፍናሥነ አካልሥነ ፈለክና ሌላ የሳይንስ ዕውቀት ነበሩ።

ምናልባት አንድ ሺህ ተማሮች ሲኖሩበት የተማሮችና የአስተማሮች ውጪ ሁሉ በፈርዖን መንግሥት ተደገፈ። መኖሪያ፣ መብልና አልገልጋይ ቢሆንም በነጻ ተቀበሉ። ይህ ኩሁሉ ጎበዝ ለሆኑት ተማሮች ነበረ።

በሙሴዎን ተቋም ታዋቂ ከሆኑት ተማሮች መካከል፦

ሮሜ መንግሥት ዘመን፣ ተቋሙ በቄሣሮች ድጋፍ እስከ 264 ዓም ይቀጥል ነበር። በዚህ ዘመን በመላው ሮሜ መንግሥት ውስጥ ሌላ ከፍተኛ ትምህርት ቤት አልነበራቸውም። በአብዛኛው በሮማውያን ዘንድ ትምህርት የተገኘው ከግል መምህር ነበርና። ሙሴዎን በቄሣሩ አውሬሊያን ትዕዛዝ በ264 ዓም እንደ ተቃጠለ ይመስላል።

የ«ሙሴዎን» ስም ከግሪክ አፈ ታሪክ ሲሆን ከኢትዮጵያ የወጡትን ዘጠኝ «ሙሳዮች» (ሴት ዘፋኞች) ለማክበር ተሰየመ። በዘመናዊ ልሳናት ደግሞ «ሙዚየም» (በተ-መዘክር) ከዚህ ተቋም ስም ደረሰ።