ኅዳር ፩
Appearance
ኅዳር ፩ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፷፩ኛው እና የመፀው ወቅት ፴፮ተኛ ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፫፻፭ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፫፻፬ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፰፻፷፬ ዓ.ም. - ለስድስት ዓመታት አፍሪቃ ውስጥ ጠፍቶ የነበረው የስኮትላንድ ተወላጅ ዶክተር ዴቪድ ሊቪንግስተን በታንጋኒካ ሐይቅ አካባቢ ኡጂጂ በሚባል ሥፍራ ላይ፣ በ ጋዜጠኛው ሄንሪ ሞርቶን ስታንሊ ተገኘ።
- ፲፱፻፴፩ ዓ.ም. - የቀድሞው ኦቶማን ግዛት ከአከተመ በኋላ፣ አዲሷን የቱርክ ሪፑብሊክን የመሠረተው ሙስታፋ ካማል አታቱርክ አረፈ።
- ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት፣ የዋቢ ሸበሌን ወንዝ ፍሰት እና ልማት ጥናት ለማካሄድ ‘ኢንግራ’ ከተባለ የዩጎዝላቪያ ተቋም ጋር የ፲ ዓመት ስምምነት ፈረመ።
- ፲፱፻፹፰ ዓ.ም.- በናይጄሪያ ታዋቂው ደራሲና የተፈጥሮ ጉዳይ ተከራካሪ ኬን ሳሮ ዊዋ (Kenule "Ken" Beeson Saro Wiwa)፣ ሰፊ የዓለም አቀፍ ተቃውሞ ቢኖርም በአገሪቱ መንግሥት ከ ሌላ ስምንት ሰዎች ጋር በስቅላት የሞት ቅጣት ተቀጣ።
- ፲፱፻፲፪ ዓ.ም.- በኮንጎ የካታንጋን ግዛት ነጥሎ በ፲፱፻፶፫ ዓ.ም. የዚያው ክልል ፕሬዚደንትነት የተመረጠውና የወቅቱ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስቴር ፓትሪስ ሉሙምባን ያስጠለፈና ያስገደለው ሞይስ ቾምቤ ተወለደ።
- ፲፱፻፴፩ ዓ.ም.- የቀድሞው ኦቶማን ግዛት ከአከተመ በኋላ፣ አዲሷን የቱርክ ሪፑብሊክን የመሠረተው ሙስታፋ ካማል አታቱርክ አረፈ።
- ፲፱፻፸፭ ዓ.ም.- የሶቪዬት ሕብረት መሪ ሊዮኔድ ብሬዥኔቭ
- ፲፱፻፹፰ ዓ.ም.- በናይጄሪያ ታዋቂው ደራሲና የተፈጥሮ ጉዳይ ተከራካሪ ኬን ሳሮ ዊዋ፣ ሰፊ የዓለም አቀፍ ተቃውሞ ቢኖርም በአገሪቱ መንግሥት ከ ሌላ ስምንት ሰዎች ጋር በሰቀላ የሞት ቅጣት ተቀጣ።
- ፳፻፩ ዓ.ም.- በደቡብ አፍሪቃ የአፓርታይድ ዘመን በስደት ላይ በዘፋኝነት በዓለም ዝና እና በምዕራባውያን ዘንድ “እናት አፍሪቃ” የሚለውን ቅጽል ስም ያተረፈችው፣ እንዲሁም በኢትዮጵያ አገራችን የጥላሁን ገሠሠን “የጥንቱ ትዝ አለኝ” የተባለውን ዘፈን በቋንቋችን በመዝፈኗ የምናውቃት ሚሪያም ማኬባ፤ በተወለደች በሰባ ስድስት ዓመቷ አረፈች።
- (እንግሊዝኛ) http://news.bbc.co.uk/onthisday/hi/dates/stories/november/10/newsid_2539000/2539561.stm
- (እንግሊዝኛ) http://www.nytimes.com/learning/general/onthisday/20081110.html
- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FO 371/154836 - Annual Report from Ethiopia for 1960
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |