አንጎላ
ከWikipedia
|
የአንጎላ ሪፑብሊክ |
||||||
|---|---|---|---|---|---|---|
|
||||||
| ዋና ከተማ | ሏንዳ |
|||||
| ብሔራዊ ቋንቋዎች | ፖርቱጊዝ | |||||
| መንግስት ፕሬዝዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር |
ሆዜ ኤድዋርዶ ዶስ ሳንቶስ ፓውሎ ካሶማ |
|||||
| የመሬት ስፋት አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.) |
1,246,700 (22ኛ) |
|||||
| ገንዘብ | ክዋንዛ | |||||
| የሰዓት ክልል | UTC +1 | |||||
| የስልክ መግቢያ | +244 | |||||
አንጎላ፣ በይፋ የአንጎላ ሪፑብሊክ (ፖርቱጊዝ: República de Angola ፣ ኪኮንጎ: Repubilika ya Ngola) በደቡብ-ምዕራብ አፍሪካ የምትገኝ ሀገር ስትሆን ከናሚቢያ ፣ ከኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ ፣ እና ከዛምቢያ ጋር ድንበር ትጋራላች። በምዕራብ ጫፍ ከአትላንቲክ ውቅያኖስ ጋር ትገናኛለች። የፖርቹጋል ቅኝ-ተገዥ ነበረች። ነዳጅ እና አልማዝ ከተፈጥሮ ሀብቶቿ የሚመደቡ ናቸው። የአንጎላ የሕግ-አስፈጻሚ ፕሬዝዳንቱን ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩን እና የሚኒስትሮች ካውንስሉን ያጠቃልላል። ሁሉም ሚኒስትሮችና ምክትል ሚኒስትሮች የሚኒስተሮች ካውንስሉን ሲሰሩ በየጊዜው እየተሰበሰቡ ስለተለያዩ የፖለቲካ ጉዳዮች ውሳኔ ይሰጣሉ። የአስራ ስምንቱ ክልሎች ከንቲባዎች በፕሬዝዳንቱ ነው የሚመረጡት። በ1992 እ.ኤ.ኣ. የወጣ ሕገ-መንግስት የመንግስቱን አወቃቀር እና የዜጎችን መብትና ግዴታ ይዘረዝራል። ፕሬዝዳንቱ መንግሥቱ በ2006 እ.ኤ.ኣ. ምርጫ ለማድረግ ዕቅድ እነዳለው ገልጸዋል። ይህ ምርጫ ከ1992 አ.ኤ.ኣ. በኋላ የመጀመሪያው ምርጫ ነው የሚሆነው። አንጎላ ውስጥ ሶስት ዋና ብሔረሰቦች ይገኛሉ። ኦቪምቡንዱ 37% ፣ ኪምቡንዱ 25% ፣ እና ባኮንጎ 13%። ሌሎች ብሔረሰቦች ቾክዌ (ሉንዳ)፣ ጋንጉዌላ፣ ንሀኔካ-ሁምቤ፣ አምቦ፣ ሄሬሮ፣ እና ዢንዱንጋን ያጠቃልላሉ። በተጨማሪም ክልሶች (አውሮፓና አፍሪካዊ) 2% ይሆናሉ። ፖርቱጋሎች አንጎላዊ ካልሆኑ ሰዎች ብዙዎቹ ናቸው።
ማውጫ |
[ለማስተካከል] ታሪክ
በአንጎላ መጀመሪያ የሠፈሩት የኮይሳን ሰዎች ነበሩ። በባንቱ ፍልሰቶች ጊዜ እነዚህ ሰዎች ወደ ደቡብ አንጎላ ሄዱ። በ1483 እ.ኤ.አ. ፖርቱጋሎች በኮንጎ ወንዝ አጠገብ ሠፈሩ። በ1575 እ.ኤ.አ. ፖርቱጋል ካቢንዳ ጋር በባሪያ ንግድ ላይ ያቶከረ ግዛት መሠረተች። በ16ኛው ክፍለ ዘመን፣ ፖርቱጋል የአንጎላ የባህር ጠረፍን ተቆጣጠረች። በተለያዩ ውሎችና ጦርነቶች የፖርቱጋል ቅኝ-ግዛት አንጎላ ተስፋፋ። የፖርቱጋል መመለሻ ጦርነትን ምክኒያት በማድረግ የደች ሪፕብሊክ ሏንዳን ከ1641 እስከ 1648 እ.ኤ.ኣ. ድረስ ተቆጣጠረች።
[ለማስተካከል] የቅኝ ግዛት ጊዜ
በ1648 እ.ኤ.ኣ. ፓርቱጋል ሏንዳን እንደገና ተቆጣጠርች። በ1650 እ.ኤ.አ. ደግሞ የተነጠቀችውን መሬት እንዳለ አስመለስች። በ1671 እ.ኤ.አ. ፑንጎ አንዶንጎ የሚባለው ቦታ ወደ ፖርቱጋል ቅኝ ግዛት ተጨመረ። ፖርቱጋል በ1670 እ.ኤ.አ. ኮንጎን እና በ1681 እ.ኤ.አ. ማታምባን ለመውረር ያደረገችው ሙከራ አልተሳካም። በ1885 እ.ኤ.አ. የበርሊን ጉባኤ የፖርቱጋል ቅኝ-ግዛት ድንበርን ከወሰነ በኋላ፣ በብሪታኒያ እና ፖርቱጋል ጥረት በኩል የባቡር-መንገድ፣ እርሻና ማዕድን ተሻሻሉ። እስከ ሀያኛው ክፍለ-ዘመን ድረስ አካባቢው ሙሉ በሙሉ በፖርቱጋል አልተመራም ነበር። በ1951 እ.ኤ.አ. ቅኝ ግዛቱ የባህር ማዶ ክፍለ-ሀገር ሆኖ ፖርቱጊዝ ምዕራብ አፍሪካ ተባለ። ፖርቱጋል አካባቢውን ወደ አምስት መቶ ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ ያህል ተኮጣጥራለች። ስለዚህም የአካባቢው ሕዝብ ነጻነት ለመውጣት ያለው ስሜት የተደበላለቀ ነበር።
[ለማስተካከል] መልከዕ-ምድር
አንጎላ፣ በ1,246,620 ካሬ ኪ.ሜ. ከኒጄር ቀጥላ ከዓለም 23ኛው ትልቅ አገር ናት። በስፋት ከማሊ ጋር ትነጻጸራለች። የአሜሪካ የቴክሳስ ክፍላገርን ሁለት ዕጥፍ ታክላለች። አንጎላ ከደቡብ በናሚቢያ፣ ከምሥራቅ በዛምቢያ፣ ከሰሜን-ምሥራቅ በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና ከምዕራብ በአትላንቲክ ውቅያኖስ ትዋሰናለች።
[ለማስተካከል] የአመራር ክልሎች
| ክልል | የሕዝብ ብዛት | የመሬት ስፋት (ካሬ ኪ.ሜ.) | ዋና ከተማ | |
|---|---|---|---|---|
| 1. | ቤንጎ | 450,000 | 33,016 | ካክሲቶ |
| 2. | ቤንጉዌላ | 600,000 | 1,788 | ቤንጉዌላ |
| 3. | ባኤ | 800,000 | 70,314 | ኩዊቶ |
| 4. | ካቢንዳ | 300,000 | 7,283 | |
| 5. | ኩዋንዶ ኩባንጎ | 140,000 | 199,049 | ሜኖንጉዌ |
| 6. | ኩዋንዛ ኖርቴ | 400,000 | 24,110 | ንዳላንታንዶ |
| 7. | ኩዋንዛ ሱል | 600,000 | 55,660 | ሱምቤ |
| 8. | ኩኔን | 200,000 | 87,342 | ኦንዲጂቫ |
| 9. | ሁዋምቦ | 1,000,000 | 34,270 | ሁዋምቦ |
| 10. | ሁኺላ | 700,000 | 75,002 | ሉባንጎ |
| 11. | ሉዋንዳ | 3,000,000 | 2,257 | ሉዋንዳ |
| 12. | ሉንዳ ኖርቴ | 103,000 | 103,000 | ሉካፓ |
| 13. | ሉንዳ ሱል | 125,000 | 77,637 | ሳውሪሞ |
| 14. | ማላንጄ | 850,000 | 97,602 | ማላንጄ |
| 15. | ሞክሲኮ | 230,000 | 223,023 | ሉኼና |
| 16. | ናሚቤ | 60,000 | 58,137 | ናሚቤ |
| 17. | ዩጂ | 800,000 | 58,698 | ዩጂ |
| 18. | ዛየር | 600,000 | 40,130 | ምባንዛ ኮንጎ |
|
||||||||||||||||||||||||||||
