ሶማሊላንድ
ከውክፔዲያ
ሶማሊላንድ እውቅና ያልተሰጠው በስራው ግን እንደ አንድ ልዑላዊ ሃገር የሚንቀሳቀስ በአፍሪካ ቀንድ በሰሜን ምስራቅ ሶማሌ የሚገኝ አካል ነው። ግንቦት ፲ ቀን ፲፱፻፹፫ ዓ/ም፥ የሶማሊላንድ ሕዝብ ነጻነቱን አውጆ ከሶማሌ ፲፰ ክፍለ ሀገራት ፭ቱን አካቶ ይዟል። ይህም በጅቡቲ፣ በኢትዮጵያ፣ በቀድሞው የጣልያን ሶማሊላንድና በአደን ባሕረሰላጤ የሚካለለውን ፻፴፯ ሺ ፮መቶ ካሬ ኪሎሜትር የሚሸፍነውን ቦታ ከሞላ ጎደል ይሸፍናል። የሶማሊላንድ ዋና ከተማ ሃርጌሳ ነው።
እውቅና ባያገኝም አካሉ ሳይዋዥቅ እንደ መንግሥት እየሠራ ይገኛል። በመስከረም ፲፰ ቀን ፲፱፻፺፰ ዓ/ም በተደረገው የከተሞች የሊቀመንበርና የሕዝብ ተወካዮች ምርጫ ኡዱብ ፓርቲ ሲያሸንፍ በተለያዩ ታዛቢዋ ትክክለኛና ነጻ ምርጫ እንደ ነበር ዘገባ ቀርቧል። ይህም ሶማሊላንድ ላቀረበችው የእውቅናው ጥያቄ ድጋፍ ይሰጣል የሚሉ ወገኖች አሉ።
|
||||||||||||||||||||||||||||
| ጅምር! (ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። እርስዎ ሊያስፋፉት ይችላሉ!) |