Jump to content

ሕግ

ከውክፔዲያ
(ከህግ የተዛወረ)

ሕግ ማለት የኅብረተሠብ ሰላምና ኑሮ ጸጥታ ለመጠብቅ ከአንድ መንግሥት የወጣ መተዳደሪያ ደንብ ነው።

ሕግም ሕግጋትም በሥነ ፍጥረት ቢሆንም የትም ይገኛሉ። የተፈጥሮ ህግጋት ጥናት እንደሚያስረዳን፣ እነዚህ ሕግጋት ከፍጥረት በላይ ተወስነው ሊጣሱ የማይችሉ ጽኑ ሕጎች ናቸው፤ ለምሳሌ የአየር ህግጋት፤ ወይንም በመሬት ስበት ክብደት ያለው ነገር ምንጊዜም ወደ ምድሪቱ ውስጥ መሃል ነጥብ አቅጣጫ የሚሳብበት መርኅ የኒውተን የግስበት ቀመር ይገልጻል። እንዲህ አይነት ሕጎች የማይጣስ መሆናቸው ከጥንት ታውቆ እንኳን በመጽሐፈ ሄኖክ መጀመርያ ክፍል ይመሰከራል። በዚያ ጽሑፍ በመንገዱ ታዛዥ ያልሆነ ኮከብ ስንኳ ቢኖር ኖሮ ጉዳት ያገኝ ነበር ይጻፋል። በሥነ አመክንዮም ዘርፍ የአስተሳሰብ ሕግጋት የተባሉት እንደ ሥነ ተፈጥሮ ሕግጋት ሊቀየሩ የማይቻላቸው ሃቆች ተቆጥረዋል።

ከተፈጥሮ ሕግጋት አልፎ፣ በብዙ ሃይማኖቶች ዘንድ ከሰዎች በላይ የሚኖሩ መንፈሳዊ ሕግጋት ይገኛሉ። የዚህ ሃሣብ በዞራስተር ሃይማኖት «አሻ»፣ በሂንዱ ሃይማኖት «ዳርማ»፣በቡዲስም «ዳማ»፣በእስልምና «ሻሪያ»ተብሏል። በአብርሃማዊ ሃይማኖቶችም «ሕገ ኦሪት» ወይም ሕገ ሙሴ በተለይም አስርቱ ቃላትወርቃማው ሕግ እንደ ተመሠረቱ ይቀበላል። ይህ «ወርቃማው ሕግ» በሌሎቹም ዋና ሃይማኖቶች ተመሳሳይ ትርጉም ተሰጥቷል።

በአለም ታሪክ፣ ብዙ ጊዜ የሰው ልጆች መንግሥታት አቁመው ለየራሳቸው ሕግጋት ወይም ሕገ መንግሥት መሠረቱ። የሰው ልጅ ህጎች ግን በሀሣዊ መሠረት ከሆኑ፣ ለጥቂቶች ሥሥት ለማገልገል ሊሆኑ ወይም ሰፊ ጉዳት ሊያምጡ ይቻላል። በድሮ ዘመን ባብዛኛው ሕግ የወጣ በንጉሥ ወይም በሌላ መሪ ቃል ይሆን ነበር። በተለይ ባለፈው 20ኛው ክፍለ ዘመን ይህን ሂደት በሥልጣኔ በማሻሻል፣ በተገዢ ሕዝቦች ምርጫ የሕግ አማካሪዎች ተመርጠው በምክር ቤት የሕግ አጻጻፍና ማረጋገጥ ሂደት በብዙዎች አገራት ሕገ መንግሥት ኑሯል። በሕጉ ወሰኖች ውስጥ በርካታ ሕጋዊ ኑሮ ምርጫዎች እንዲገኙ ስለ ሕዝቡ ነፃነት የሚሻ በማለት ነው።

«የሕግ ቀለም» ማለት የሕግ ወኪሎች የተባሉት ወይም አስመሳዮች አሳምነው በሐሳዊ ሕግ ወይም በወንጀል እርምጃ ሲወስዱ ነው። እንዲህ እንዳይደረግ፣ የሕግ የበላይነት ማለት ማናቸውም ሰው ወይም ወኪል በሕጋዊ መሠረት ከሆነ ከሕጉ ሥር ተጠቅልሎ ይገኛል።