የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ
Appearance
(ከማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን የተዛወረ)
የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ (ማ.ስ.ኤ.) በኢትዮጵያ መንግሥት በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ስር የሚገኝ ኤጀንሲ ወይም ባለስልጣን ሲሆን ተልዕኮው ለኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ዕድገት አሰሳ የሚያገለግሉ የሕዝብ ቆጠራ፣ የዋጋ መረጃ ማሰባሰብ፣ የቤተሰብ ፍጆታና ወጪን ማጥናትና ሌሎች ተመሳሳይ ተግባሮችን ማከናወን ነው። በተጨማሪም ኤጀንሲው በዘርፉ ባለሙያዎችን የማሰልጠን ኃላፊነት አለበት። በአሁኑ ጊዜ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ሳሚያ ዘካሪያ ናቸው።
ከየካቲት ፴ ቀን ፲፱፻፹፩ ዓ.ም. በፊት ኤጀንሲው የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ቢሮ በመባል ይታወቅ ነበር። በአሁኑ ጊዜ ኤጀንሲው በሚከተሉት ፳፭ ቦታዎች ቅርንጫፎች አሉት፦ አዲስ አበባ፣ አምቦ፣ አርባ ምንጭ፣ አሰበ ተፈሪ፣ አሳይታ፣ አሶሳ፣ አዋሳ፣ ባህር ዳር፣ ደብረ ብርሃን፣ ደሴ፣ ድሬ ዳዋ፣ ጋምቤላ፣ እንደ ሥላሴ፣ ጋምቤላ፣ ጎባ፣ ጎንደር፣ ሐረር፣ ሆሳዕና፣ ጅጅጋ፣ ጅማ፣ መቀሌ፣ ሚዛን ተፈሪ፣ ናዝሬት፣ ነገሌ፣ ነቀምት እና ሶዶ።[1]
አገር አቀፍ የሕዝብና መኖሪያ ቆጠራ እ.ኤ.አ. በ1984፣ 1994፣ 2007 የተከናወነ ሲሆን የመጨረሻዎቹ ሁለት ቆጠራዎች ዝርዝር መረጃ በኤጀንሲው ድረ-ገጽ ላይ ይገኛል።
- ^ "Branch offices" Archived ኦገስት 16, 2010 at the Wayback Machine, Central Statistical Agency website (በነሐሴ ፯ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. የተወሰደ) (እንግሊዝኛ)
ደሳለ
- ይፋ ድረ-ገጽ (እንግሊዝኛ)