Jump to content

ሩድራይግ

ከውክፔዲያ

ሩድራይግ ማክ ዴላ (ወይም ሩግራይድ፣ ሩግሩዊድ) በአየርላንድ ልማዳዊ አፈ ታሪክ ዘንድ ከፊር ቦልግ የአየርላንድ ፪ኛ ከፍተኛ ንጉሥ ነበር። ሩድራይግ የዴላ ልጅና የስላንጋ ወንድም ነበር። ሚስቱ ሊበር ተባለች።

5000 ፊር ቦልግ አይርላንድን በ1130 መርከቦች በወረሩበት ጊዜ (1538 ዓክልበ. ግድም) ሩድራይግ ከዴላ ሌላ ልጆች ጋር ሻለቃ ነበረ። ሩድራይግና ወንድሙ ጌናን ከንዑስ-ወገናቸው ፊር ዶምናይን ጋር ደሴቱን በእንበር ዶምናይን (አሁን ደንድረም ወሽመጥ) ገቡ። የሩድራይግ ክፍል ኡልስተር የሚባል ክፍላገር ሆነ (በአሁኑ ስሜን አይርላንድ)። ደግሞ ወንድሙ ስላንጋ ከ1 ወይም 2 አመት በኋላ ዓርፎ ሩድራይግ ከፍተኛ ንጉሥ ሆኖ ተከተለው። ነገር ግን ከሁለት አመት በኋላ ሩድራይግ ዓረፈ። ዜና መዋዕሎቹ እንደሚሉ፣ «በብሩ ነ ቦነ ወደቀ» ሲሉ መውደቁ በውግያ እንደ ነበር ወይም በአደጋ እንደ ሞተ ግልጽ አይደለም። ወንድሞቹ ጋንና ጌናን ተከተሉት።

ቀዳሚው
ስላንጋ
አይርላንድ (ኤልጋ) ከፍተኛ ንጉሥ
1536-1534 ዓክልበ. (አፈታሪክ)
ተከታይ
ጋንጌናን