ሰዴ

ከውክፔዲያ

ሰዴ ወረዳ በ ምስራቅ ጎጃም ዞን የሚገኝ ወረዳ ነው። በ2009 አ.ም 16 የደጋ ቀበሌዎችን በመያዝ ከ ሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ተቀንሶ የተመሰረተ ወረዳ ነው። የወረዳው ከተማ ሰዴ ይባላል። ሰዴ ከተማ ከ ሞጣ ያለው የመስመር ርቀት በ ቀራንዮ መስመር 32 ኪሎሜትር በ ቻክ መድኃኔዓለም በድሮው የእግር መንገድ 16 ኪሎሜትር ነው። ከተማው በቀደሙት ሰዎች ሰዴ ጊዎርጊስ እየተባለ ይጠራል። ይህ አጠራር በከተማው ከሚገኘው ጥንታዊ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዎርጊስ ቤተክርስቲያን ጋር የተያያዘ ነው። ሰዴ እሰከ 1974 በ ሞጣ አውራጃ ስር የ ሁለት እጁ እነሴ ወረዳ አስተዳደር መቀመጫ ነበረች። የ ሰዴ ወረዳ በሰሜን የ ሁለት እጁ በምዕራብ ቢቡኝ በደቡብ ደባይ ጥላትግን በምስራቅ ጎንቻ ሲሶ እነሴ ያዋስኑታል ። በወረዳው ሁለት ባንክ ማለትም መንግስታዊው የ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የግል ባንክ የሆነው አቢሲኒያ ባንክ2011 አ.ም ጀምሮ አገልግሎት እየሰጡ ነው። በወረዳው ሶስት ጤና ጣቢያዎች ሰዴ ፣ ከርነዋሪ እና ጎይባ አግልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ።

ሰዴ ከተማ 1992 ዓ.ም የ ውሃ በ 2000 ዓ.ም ደግሞ የመብራት ተጠቃሚ ሆናለች ።

አየር ንብረት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የ ሰዴ ከተማ ከባህር ወለል በላይ 2550 ሜትር ከፍታ ላይ ትገኛለች። ከተማዋን ሰዴን ጨምሮ አብዛኛው ቀበሌዎች ደጋማ አየር ንብረት አላቸው። የ ሰዴ ከተማኬክሮስ እና ኬንትሮስ ( ላቲቲዪድ እና ሎንግቲዪድ መገኛው በ10°55′ ሰሜን ኬክሮስ እና 37°53′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ነው።


ሕዝብ ብዛት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በ 2011 አም በነበረው መረጃ የወረዳው ህዝብ ብዛት 101763 ነበር። በ1999 አም ማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ ባደረገው የ ሕዝብና ቤቶች ቆጠራ በ ሰዴ ከተማ 2309 ( ሁለት ሺ ሶስት መቶ ዘጠኝ ) ጠቅላላ ሕዝብ ነበረ። ከነኚም መካከል 1296 ወንድ ሲሆኑ ቀሪዎቹ ደግሞ ሴቶች ነበሩ። ከ 1999 አም በፊት 1987 አም በተደረገው አገር አቀፍ ሕዝብና ቤቶች ቆጠራ በ 408 አባዎራዎች ቤት የ ሰዴ ጠቅላላ ሕዝብ 1345 ነበረ። ከእነዚህ 533 ወንድ ሲሆኑ 812 ደግሞ ሴቶች ነበሩ። በዚህ ቆጠራ መሰረት አብዛኛው የ ከተማዋ ሕዝብ 94.6 % ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሀይማኖት ተከታይ ሲሆን 5.4% ደግሞ ሙስሊም ነበሩ። ሰዴ የ 24 ሰዐት የመብራት አገልግሎት ተጠቃሚ ከሆነች ጀምሮ የ የከተማዋ ህዝብ ብዛት ጨምሯል ። በተለይ ከተማዋ ራሷን ችላ የወረዳ ማዕከል ከሆነች ጀምሮ የከተማዋ ህዝብ ብዛት በአያሌ ጨምሯል።

ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ የሰዴ ወረዳ አስተዳዳሪዎች በቅደም ተከተል[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. አቶ አብርሀም አያሌው
  2. አቶ መላኩ ከበደ
  3. ደመቀ ንጉሴ

ስዩም ይዘንጋው ድንቁ (talk) 20:29, 8 ዲሴምበር 2020 (UTC)