Jump to content

ሳይንስ

ከውክፔዲያ
(ከሳ ይ ን ስ የተዛወረ)

ሳይንስ የሚለው ቃል ከላቲን scientia (/ስኪየንቲያ/)[1] የመጣ ሲሆን ትርጉሙም «ዕውቀት» ማለት ነው። ሆኖም ግን በአሁኑ ዘመን ሳይንስ ማለት ዕውቀት ማለት አይደለም። ሳይንስ የዕውቀት ዘርፍ ነው እንጂ ሁሉ ዕውቀት ሳይንስ አይደለም። ፍልስፍና ለምሳሌ ሳይንስ አይደለም ምንም እንኳ ዕውቀት ቢሆንም። ሂሳብ ለምሳሌ ሳይንስ አይደለም ዕውቀት ይሁን እንጂ።

ሳይንስ ማለት በተግባር ሊፈተኑ በሚችሉ ማብራሪያዎችና እንዲሁም ትንቢቶች መንገድ እውቀትን የሚገነባ እና የሚያደራጅ መዋቅር ነው። [2] «ሊፈተን የሚችል» ሲባል እውነትነቱ ሊረጋገጥ የሚችል ማለት ሳይሆን ውሸት አለመሆኑ ሊረጋገጥ የሚችል ማለት ነው። በሁለቱ መካከል ከፍተኛ ልዩነት አለ፣ ሳይንስን ከሃይማኖትና ከሌሎች የዕውቀት ዘርፎች የሚለየው ይህ ወሳኝ ልዩነት ነው።

ሳይንስ ባጠቃላይ መልኩ የሳይንሳዊ ዘዴ ተብሎ የሚታወቀውን የምርምር መንገድ ይከተላል። መንገዱ በራሱ ገጽ ላይ የተብራራ ስለሆነ እዚህ ላይ መመለስ አያስፈልግም።

ሲውዶ-ሳይንስ ወይም ሐሣዊ ሳይንስ በተቀራኒ የተመሠረተው በ«እኩያ ግፊት» (ንቀት ይሉኝታ) እና ከቡድን ውግዘት ላይ ነው እንጂ በሳይንሳዊ ዘዴ ላይ በተለይም የሙከራ ውጤት በጭራሽ በቅንነት በማስረዳት ላይ አይሆንም። ባለፈው ክፍለዘመን ለፖለቲካ ብለው ለዚህ አይነት ሐሣዊ ሳይንስ ገንዘብ ያወጡት መንግሥታት ለምሳሌ ናዚ ጀርመን እና የሶቪዬት ሕብረት እንደ ነበሩ ተባለ፤ አሁንም ቢሆን ብዙ ሐሣዊ ዜና ስለ ፖለቲካ ሲወጣ ነው በተባለበት ወቅት እንኖራለን። የአንዱ መንግሥት «ሳይንስ» ለሌላው «ሲውዶ-ሳይንስ» ሊሆን ይችላል፤ ለምሳሌ የቱርክ ሙስታፋ ኬማል አታቱርክ መንግሥት ከ1928-1930 ዓም የፀሐይ ቋንቋ ሃልዮን ይደግፍ ነበር።

ግርጌ ነጥቦችና ዋቢ ጽሁፍ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
  1. ^ «ሳይንስ» የሚለው አጠራር ከእንግሊዝኛው ቃል «science» ነው፤ ለዚሁም አጠራር ታሪካዊ ምክንያት በተጨማሪ Cን እና ታላቅ የአናባቢ መፈራረቅን ያንብቡ።)
  2. ^ http://www.m-w.com/dictionary/science