የፀሐይ ቋንቋ ሃልዮ

ከውክፔዲያ

የፀሐይ ቋንቋ ሃልዮ (ቱርክኛ፦ Güneş Dil Teorisi) በ1920ዎቹቱርክ አገር የተደረጀ ሃልዮ ነበር። ይህም ሃልዮ ዛሬው እንደ ሀሣዊ የቱርክ ጎሰኛ አስተያየት ይቆጠራል። በዚህ ሃልዮ ዘንድ፣ በቅድመ-ታሪክ የሰው ልጅ ልሳናት ሁሉ ከአንድ ቅድመ-ቱርክኛ ቋንቋ እንደ ተወለዱ ይታመን ነበር። ይህም ቅድመ-ታሪካዊ ቋንቋ በድምጽ በተለይ ለዘመናዊ ቱርክኛ ተመሳሳይነት ስለነበረው፣ ሌሎቹ ልሳናት ሁሉ ከቱርክኛ ሥሮች እንደ ደረሱ ለማሳየት የሞከረ ግምት ነበር። ከዚህ በላይ፣ በማእከለኛ እስያ የተገኙት ምእመናን የፀሐይን ከሃሊነትና ሕይወት-ሰጪ ጸባይ ለማክበር ፈልገው፣ ይህን በማድረግ ቀድሞ ያሰሙት የነበረው እንቶ ፈንቶ ተለውጦ ያንጊዜ ሥነ ስርዓት ወዳለበት አነጋገር ተቀየረ፣ ቋንቋውም ተወለደ፣ ስለዚህ «የፀሐይ ቋንቋ» ነው የሚሉት።[1]

መነሻ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በዚሁ ሃልዮ ተጽእኖዎች ውስጥ፦

  • ፈረንሳይ ታሪክ ጸሐፊ ኢሌር ደ ባረንቶን ያቀረበው አስተያየት በመጽሐፉ "L'Origine des Langues, des Religions et des Peuples" («የልሳናት፣ የሃይማኖትና የአሕዛብ መነሻ»)፣ የዓለም ቋንቋዎች ሁሉ ከሱመርኛ ጽሑፍ እንደ ተነሡ ገመተ።[2]

የቱርክ ሪፐብሊክ መሥራችና መጀመርያው ፕሬዚዳንት፣ ሙስታፋ ኬማል አታቱርክ ይህን ግምት ይፋዊ ድገፋና ንብረታዊ ድገፋ ከመስጠቱ በላይ፣[4] በራሱ በኩል ደግሞ በአደረጃጀቱ ታላቅ አስተዋጽኦ ያቀረበ ሆነ።[5]1928 ዓም ጀምሮ አታቱርክ እስካረፈበት ዘመን እስከ 1930 ዓም ድረስ በቱርክ አገር በይፋ ተቀባይነት ነበረው። ከአታቱርክ ዕረፍት ጀምሮ ግን ተተወ።

እምነቶች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በ1928 ዓም በአሜሪካዊው ጋዜጣ ዘ ኒው ዮርክ ታይምዝ አንቀጽ ስለ አንካራ ዩኒቬርሲቴ አዲስ ክፍል፣ «የቋንቋ፣ የታሪክና የመልክዓ ምድር ትምህርት ቤት» በመግለጽ፦

[2]

ሱመርራውያን፣ ቱርኮች ሆነው፣ ከመካከለኛ እስያ ተነሥተው፣ ስለዚህ ልሳናት ሁሉ ደግሞ እዚያ ተጀመሩና መጀመርያ በቱርኮቹ ተጠቀሙ። እንዲያውም መጀመርያው ቋንቋ እንዲህ ተፈጠረ፦ ቅድመ-ታሪካዊ ሰው ልጅ፣ ማለት ቱርኮቹ፣ ከሁሉ ቅድማዊ በሆነ ደረጃ ሲሆኑ፣ የፀሐይ ሥራ ትኩረታቸውን ስቦ፣ በጎውና ክፉው ሁሉ የመነጨበት አምላክ ተቆጠሩት። ከዚያ ብርሃን፣ ጥላ፣ ሙቀትና እሳት መጣላቸው፣ ከሱ ጋር የጊዜ ሀሣቦች ሁሉ ተሳሰሩ፤- ቁመት፣ ርቀት፣ እንቅስቃሴ፣ ስፋት፣ ስሜታቸውንም ለመግለጽ ፀሐይ እንግዲህ ከነገሮች ሁሉ ይልቅ ተሰየመ። ስሙም «አግ» ነበር፤ ከዚህም ቃል ዛሬው የሚናገሩት ቃላት ሁሉ ተወለዱ። ይህ ባጭሩ «የፀሐይ ቋንቋ ሃልዮ ነው፤ በቱርክ አገር ታሪክ አዲስ አስተሳሰብ ዘንድ፣ በአዲሱ የአንካራ ትምህርት ቤት ይማራል።

ባጭሩ፣ የሥልጣኔና የሰው ልጅ ልሳናት ምንጭ በፀሐይ አማካይነት ነበር በማለት የተመሠረተ አስተያየት ሲሆን፣ በሃልዮው ዘንድ የተሠለጠኑት ቋንቋዎች ሁሉ አባት ቱርክኛ ይሆን ነበር።[6]

አንዳንድ ቃላት ሀሣዊ የቱርክኛ ታሪክ ተሰጡ፣ ለምሳሌ ያሕል፦ እንግሊዝኛ school /ስኩል/ (ትምህርት ቤት) ከቱርክኛ ቃል okul ኦኩል፤ እንግሊዝኛ God /ጎድ/ (አምላክ) ከቱርክኛ kut /ኩት/ (በረከት)፤ እንግሊዝኛ Bulletin /ቡለትን/ (ማስታወቂያ) ከ belleten /በለተን/ (በልብ መማር); Electric (ኤሌክትሪክ) ከውግርኛ yaltrık /ያልትርክ/ (በራ)።[5][7]

በቋንቋ ሊቅ ጊልዓድ ዙከርማን ዘንድ፣ «አታቱርክ የፀሐይ ቋንቋ ሃልዮ የደገፈው፣ የቱርክኛ ቋንቋ ባለሥልጣኖች ሊወግዱ ያልቻሉ አረብኛና ፋርስኛ ቃላት ለማጽደቅ እንደ ሆነ ይቻልል። በዚህ አድራጎት፣ ከውጭ አገር ልሳናት ለተበደረ ለያንዳንዱ ቃል አዲስ ዘይቤ ማቅረብ አለመቻላቸውን ተተካ።»[8]

ነጥቦች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

<div class="reflist references-column-count references-column-count-2" style="

list-style-type: decimal;">
  1. ^ Aytürk, İlker (November 2004). "Turkish Linguists against the West: The Origins of Linguistic Nationalism in Atatürk's Turkey". Middle Eastern Studies (London: Frank Cass & Co (Routledge)) 40 (6): pp.1–25. doi:10.1080/0026320042000282856. ISSN 0026-3206. OCLC 86539631. 
  2. ^ "Turks Teach New Theories". New York Times (Istanbul). 1936-02-09. http://select.nytimes.com/gst/abstract.html?res=F70914FC395F167B93CBA91789D85F428385F9. 
  3. ^ Laut, Jens Peter (2002). "Noch einmal zu Dr. Kvergić" (in German) (PDF reprinted online). Turkic Languages (Wiesbaden, Germany: Harrassowitz Verlag) 6: pp.120–133. ISSN 1431-4983. OCLC 37421320. http://www.freidok.uni-freiburg.de/volltexte/1830/pdf/Laut_Noch_einmal_zu_Dr_Kvergic.pdf በ2007-12-05 የተቃኘ. 
  4. ^ See Speros Vryonis. The Turkish State and History: Clio meets the Grey Wolf, 2nd Ed. Thessaloniki: Institute for Balkan Studies, 1993.
  5. ^ Lewis, Geoffrey (2002). The Turkish Language Reform: A Catastrophic Success. Oxford University Press. 
  6. ^ Cemal Kafadar, Between Two Worlds: The Construction of the Ottoman State, Published by University of California Press, 1996. pg 163.
  7. ^ Lewis, Geoffrey (11 February 2002). "The Turkish Language Reform: A Catastrophic Success". Archived from the original on 12 January 2007. በ27 November 2015 የተወሰደ.
  8. ^ Zuckermann, Ghil’ad (2003), ‘‘Language Contact and Lexical Enrichment in Israeli Hebrew’’ Archived ፌብሩዌሪ 1, 2014 at the Wayback Machine, Houndmills: Palgrave Macmillan, ISBN 1-4039-1723-X, p. 165.

ተጨማሪ ምንጮች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

መለጠፊያ:Refbegin

መለጠፊያ:Refend