Jump to content

በር:ምህንድስና

ከውክፔዲያ
(ከበር:ኢንጂኔሪንግ የተዛወረ)
ተግባራዊ እውቀት

ተጋባራዊ ዕውቀትሳይንስኢንጂነሪንግ ጥናት በመነሳት ሰውንና ከባቢውን ሊጠቅሙ ይችላሉ የተባሉ መሳሪያዎችን፣ ዕደ ጥበባትን፣ ዘዴዎችን፣ ሥር ዓቶችን ለማቀናበር የሚያግዙ መንግዶችን በተግባር ላይ የሚያውል የዕውቀት ዘርፍ ነው። ተግባራዊ ዕውቀት አዲስ ነገር አይደለም። ከ2 ሚሊየን አመት በፊት ጀምሮ ሰዎች የድንጋይ መሳሪያን በስራ ላይ እንዳዋሉ ይታዎቃል። ሌሎች ቀደምት ቴክኖሎጂወችን ብንመለከት እሳትልብስ እና እርሻን በምሳሌነት ይጠቀሳሉ። እነዚህ ዕውቀቶች ለዘላለም ከሰው ጋር የነበሩ ቢመስሉም፣ ዕውነታው ግን ሰው በአንድ ዘመን የፈጠራቸውና ከዚያ በፊት ያልነበሩ የዕውቀት ዘርፎች ናቸው።

በሰው ልጅና በከባቢው አለም መካከል ያለውን ግንኙነት ቴክኖሎጂ በስር ነቀል ሁኔታ እንደሚለውጠው መረዳት ቀላል ነው። ለምሳሌ በጥንቱ ዘመን በባህሮችና ውቅያኖሶች የሚንሳፈፉ ታንኳወች መፈጠር፣ እንዲሁም የተሽከርካሪ መንኮራኩር መፈልሰፍ፣ የሰው ልጅ ከቦታ ቦታ የሚያደርገውን ጉዞ በብርቱ ሁኔታ ቀይሯል። በቅርቡ እንኳ የባቡርአውሮፕላን እና የጠፈር መንኮራኩር መፈጠር በሰው ልጅ ህይወት ላይ ከፍተኛ ለውጥን አስከትለዋል። የተጻፈ ቋንቋማተሚያ ቤትስልክ እና ኢንተርኔት በየዘርፉ የሰውን ልጅ ህይወት በአጠቃላይ መልኩ መቀየራቸው አሌ የማይባል ነው።