Jump to content

ቢላል

ከውክፔዲያ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው ያ አላህ አንተ ካሳወቅከን በስተቀር እውቀት የለንምና ጠቃሚ እውቀትን ትሰጠን ዘንድ እንማጸንሀለን ::አሜን

ቢላል ኢብን ረባህ
بلال بن رباح
ሃበሻዉ ሙአዚን
Frameless
Frameless
(16ተኛዉ ክፍለ ዘመን, ከቱርክ), የሚገልጸዉ ቢላል ከአባ ላይ ሁኖ አዛን እያደረገ ወይንም ለስግደት እየተጣራ.
የትውልድ ቀን 580/3/5 AD
የትውልድ ቦታ መካ,ሀጃዝ ከተማ(Mecca, Hejaz)
Ethnicity አፍሮ-አረብ (Afro-Arab) የሀበሻ ልጅ ሀበሻ
የሚታወቅበት Being a loyal companion of Muhammad and የመጀመርያ አዛን አድራጊ[1][2]
ስራ Secretary of Treasure of The Islamic State of Medina
Died 640/3/2 AD
አባት ራባህ (Rabah)
እናት ሀማም (Hamamah)
ሚስት ሂንድ (Hind)
ሀይማኖት ኢስላም(Islam)


ቢላል በባርነት

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ቢላል ኢብን ረባህ በአረብኛ بلال بن رباح‎. የሚታወቅበት ስሞቹም ቢላል አል ሃበሽይ፣ ቢላል ኢብን ሪያህ፣እና ቢላል ኢብን ረባህ. ቢላል ታማኝ እና ኢማንነኛ ነበር በነብዩ ሙሀመድ ልብ ዉስጥ ልዩ ቦታ ነበረዉ. ቢላል የተወለደዉ ነብዩ ሙሀመድ ከተወለዱበት ቅዱስ ከተማ መካ ዉስጥ ነዉ የተወለደዉ ቤተሰቦቹ ገን በኢትዮጵያ ደማስቆ በምትባል ከተማ ዉስጥ ነዉ ተነስተዉ ወደ መካአቢሲኒያ ኢትዮፕያ ዉስጥ በባርነት ተሽጠዉ ነበር የሀዱት የሚባለዉ. ቢላል ከባርነት ላወጣዉ እስልምና በሙአዚንነት ስያገለግል ነዉ የሞተዉ. በሙአዚንነቱ በእስልምና ታሪክ የመጀመርያዉ ሙአዚን ነዉ. ለመጀመርያ ሙአዚንነቱ የተመረጠዉ በነብዩ ሙሀመድ ነበር. ቢላል ከባርነት የወጣዉ በአቡበክር ነበር. ምክንያቱም ቢላል ባርያ ስለነበር አሳዳሪዉ ኡመያህ ከእስልምና ዉጣ በነላት እና ኡዛ እመን ሲል በመካ በርሃ በጸሀይ በተቃጠለ አሽዋማ መሬት ላይ አስሮ ሆዱ ላይ ትልቅ ደንጋይ እየጣለ ሲቀጣዉ አሀዱን አሀድ እያለ ስቃዩን ለአላህ ስያደርግ ስቃዩን ለማስቆም አቡበክር ሰዉ ልኮ በፈለገዉ ያህል ገንዘብ እንዲገዛዉ ጠየቀዉ ኡመያህም እሽ ሲል ሸጠለት. ከዛም አቡበከር ለራሱ ባርያ ሊአደርገዉ አልፈለገም ነጻነትን ሰጠዉ. ከዛን ቀን ቡሃላ ባርነቱ አብቅትዋል. ቢላል ድምጸ መርዋው ህዝቦቹን በሚያምር ድምጹ የሚጣራ ይሉታል. ቢላል የሞተዉ በ638 እስከ 642 ባለዉ ነው. እስልምናን የተቀበለዉ የአስራ ስድስት አመት ወጠጤ እያለ ነበር. በስልምና የቢላል ታሪክ እስልምና ከመጣ ቡሃላ እንዴት ባርነት እንደቀነሰ ነዉ.

=እንዴት ወደ እስልምና እንደገባ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ቢላል ኢብኑ ረባህ የምስጋና እና የሙገሳ ቃላትን ሲሰማ አንገቱን ይደፋ ነበር እናም አይኖቹን በትዝታ ገርበብ አድርጎ ትናንት ባሪያ የነበርኩ ሀበሻ ነኝ ይላል። እነሱ ግን የእኛ ልዑል ብለው ነበር የሚጠሩት። ኡመያ ኢብን ኸለፍ በመባል የሚታወቅ ቁረይሽ ባሪያ የነበረው ቢላል ነብዩ ሙሀመድ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም በነብይነት የመላካቸው ወሬ የመካን ህዝብ ሲያተራምስ ከቢላል ጆሮ ደረሰ። የቢላል አሳዳሪ ከእንግዶቹ ጋር ስለ ነብዩ መላክ እና ጣኦታቸውን እንደሚቃወም በንዴት እየተብሰለሰለ እና ሴራ እያውጠነጠነ ሲናገር ሙሐመድ ስለተንሱበት አላማ እና ምን እያሉም እንደሚያስተምሩ ሊቀነጭብ ቻለ። አዲስ የመጣው ዲን ለአካባቢው እንግዳ እና ስር ነቀል ለማምጣት ያለመ ሙሀመድም ምንም እንኳን ነብይ ነኝ ብለው በመናገራቸው ተቃውሞ የገጠማቸው ቢሆንም ታማኝ :እውነተኛ እና በስነ ምግባር የታነጹ መሆናቸውን ከጠላቶቻቸው ቁንጮዎች አንደበት አድምጧል። «ሙሀመድ አንድም ቀን ዋሽቶ አያውቅም: ጠንቋይም ሆነ እብድ አልነበረም:... ዛሬ ግን እኛ እርሱን በነዙህ ነገሮች መጥራት ይኖርብናል። ወደ እርሱ የሚጎርፉትን ሰዎች መግታት የምንችለው በዚህ መንገድ ነው።» በማለት ዚዶልቱ ቢላል ታዝቧል።

እምነቱን ሲገልጽ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ሙሐመድን የሚቃወሙት በቅድሚያ የአባቶቻቸውን እምነት ቀጣይነት ለማረጋገጥ ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ የቁረይሽን የበላይነት የሚያከስም መስሎ ስለተሰማቸው ነው። ቁረይሽ በመላው አረብ ለጣኦታዊ እምነት ማዕከል በሆነችው በመካ የሚገኝ ነገድ በመሆኑ ተፈሪነቱ እና ከበሬታው የላቀ ነበር። በ 3ኛ ደረጃ በኒ ሀሽም ተብሎ በሚታወቀው የነብዩ ሙሐመድ የዘር ሀረግ ቤተሰብ ላይ ያሳደሩት ቅናት እና ምቀኝነት ነበር። ከበኒ ሀሽም ቤተሰብ ነብይ እና መልእክተና መምጣቱን እንደ ሽንፈት ቆጥረውታል ? ሁሉም ጎሳ እና ቤተሰብ ከራሱ ወገን ነብይ እንዲወጣ ይመኝ ነበር። ከ እለታት አንድ ቀን ቢላል ኢብኑ ረባህ የኢማን ብርሀን ፈነጠቀበት : ምርጫውን ይፋ ማድረግ እንዳለበት ወሰነ። ወደነብዩ ሙሀመድ በመሄድም ለኢስላም እጁን መስጠቱን ይፋ አደረገ። የቢላል መስለም በመካ ምድር ተሰማ። የበኒ ጁመህ መሪዎች በቁጣ ተወጠሩ : በተለይ አሳዳሪው የኢስላም ጠላት ኡመያ ኢብን ኸለፍ ሀበሻዊ ባሪያው መስለሙ እንደ ታላቅ ነውር እና ንቀት ቆጥሮታል። ለዚህም እንዲህ አለ «-ይህ ኮብላይ ባሪያ በመስለሙ ጸሀይ ተመልሳ የምትጠልቅ አይመስለኝም...» ሲል ቁጭቱን ገለጸ።

በእምነቱ የደረሰበት ችግር

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ቢላል ግን ለኢስላም ብቻ ሳይሆን ለመላው የሰው ዘር የሚያኮራ አቋም ከመውሰድ ወደ ሁዋላ አላለም። አላህ የአንድ ሰው የቆዳ ቀለሙ መጥቆር ከፍተኛውን የኢማን ደረጃ ለማግኘት የሚያግደው እንደማይሆን በቢላል ተምሳሌነት አስተምሯል። ቢላል ለዘመኑ ሰዎች እና ከ እሱ በሁዋላ ለመጣው ትውልድ እንዲሁም እምነቱን ለሚጋሩት እና ለማይጋሩትም ወገኖች ያስተማረው ትምህርት ቢኖር የህሊና ነጻነት እና ሉአላዊነት ምድርን የሞላ ንዋይም ሆእን አሰቃቂ ቅጣት ሊበግረው እንደማይችል ነው። ቢላል እርቃኑን በትኩስ አሸዋማ መሬት ላይ እንዲንከባለል እና ቋጥኝ ድንጋይም ደረቱ ላይ እንዲጫን ተደርጓል። ግን እምነቱን ሊቀይር አልፈቀደም። በተከታታይ እና በተደጋጋሚ ኢ -ሰባአዊ ድርጊት ተፈጽሞበታል። የቁረይሽ ሹማምንት አንድን ባሪያ ሊያሳምኑ እና ወደ ቀድሞው እምነቱ ሊመልሱት ባለመቻላቸው ቁጭት እና ሀፍረት ስለተሰማቸው ክብራቸውን ለመጠበቅ ሲሉ ቢላል ቢያንስ ቢያንስ ስለ አማልክቶቹ ጥቂት በጎ ነገር እንዲናገር ቢጠይቁትም አሻፈረኝ አለ። ህይወቱን ከስቃይ ምናልባትም ከሞት ለማዳን ቢያንስ ስለ አማልክቶቻቸው ከልቡ እንኳ ባይሆን ማመስገን በቂ ነበር። ታላቁ ቢላል ግን ከስጋዊ ህመም መንፈሳዊ የበላይነትን በመምረጡ ለጠላቶቹ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም። ይልቁንም በተደጋጋሚ አሀድ አሀድ ... በማለት የአምላክን አንድነት ያውጅ ነበር። ላት እና ኡዛ የተሰኙ ጣኦታትን እንዲያወሳ ያለመታከት ይጠይቁታል። መልሱ ግን አሁንም አሀድ ...አሀድ ...ነበር። እኛ የምንለውን ደግመህ በል በማለት ይገርፉታል : በምጸታዊ ቃልም እናንተ የምትሉትን ለመናገር ምላሴ አይችልም ይላቸዋል .... ከዛም ህመሙን ለመቀነስ እና ነጻነቱብ ለመስጠት አቡበከር ከኡመያ ቢላልን ገዛዉ ከዛም ነጻ አወጣዉ.

  1. ^ "Slavery in Islam." BBC News. BBC, 2009. Web. 2013.
  2. ^ Riz̤vī, Sayyid Sa'eed Ak̲h̲tar. Slavery: From Islamic & Christian Perspectives. Richmond, British Columbia: Vancouver Islamic Educational Foundation, 1988. Print. ISBN 0-920675-07-7 Pg. 35-36