ነሐሴ ፭
Appearance
ነሐሴ ፭ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፴፭ ኛው ዕለት ሲሆን የክረምት ወቅት ፵ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ቀን በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ሉቃስ ፴፩ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ማቴዎስ፤ ማርቆስ እና ዮሐንስ ደግሞ ፴ ዕለታት ይቀራሉ።
- ፲፱፻፵፬ ዓ/ም - በዮርዳኖስ ሐሺሚ ንጉዛት ንጉሡ ታላል በአዕምሮ ሕመምተኛነት ምክንያት በአገሪቱ ምክር ቤት ሸንጎ “ለሥልጣን ብቃት የላቸውም" ተብለው ሲሻሩ ገና አሥራ ስምንት ዓመት ያልሞላቸው ልጃቸው አልጋወራሹ በንጉሥነት እንደተኳቸው ይፋ ተደረገ። ንጉሥ ሁሴን የልደታቸው ዕለት ኅዳር ፯ ቀን ፲፱፻፵፮ ዓ/ም የንግሥ ስርዓታቸው ተከናወነ።
- ፲፱፻፺፩ ዓ/ም - በአውሮፓ እና በእስያ አኅጉራት እስከ ፫፻፶ ሚሊዮን የሚቆጠሩ በአውሮፓውያን አቆጣጠር የምዕተ ዓመቱን የመጨረሻ ድፍን የፀሐይ ግርዶሽ ተመልክተዋል።
- (እንግሊዝኛ) http://en.wikipedia.org/wiki/August 11