Jump to content

ነሐሴ ፭

ከውክፔዲያ
(ከነሐሴ 5 የተዛወረ)

ነሐሴ ፭ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፴፭ ኛው ዕለት ሲሆን የክረምት ወቅት ፵ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ቀን በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ሉቃስ ፴፩ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ማቴዎስማርቆስ እና ዮሐንስ ደግሞ ፴ ዕለታት ይቀራሉ።


ታሪካዊ ማስታወሻዎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  • ፲፱፻፵፬ ዓ/ም - በዮርዳኖስ ሐሺሚ ንጉዛት ንጉሡ ታላል በአዕምሮ ሕመምተኛነት ምክንያት በአገሪቱ ምክር ቤት ሸንጎ “ለሥልጣን ብቃት የላቸውም" ተብለው ሲሻሩ ገና አሥራ ስምንት ዓመት ያልሞላቸው ልጃቸው አልጋወራሹ በንጉሥነት እንደተኳቸው ይፋ ተደረገ። ንጉሥ ሁሴን የልደታቸው ዕለት ኅዳር ፯ ቀን ፲፱፻፵፮ ዓ/ም የንግሥ ስርዓታቸው ተከናወነ።
  • ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - ቻድፈረንሳይ ቅኝ ግዛትነት ነፃነቷን አወጀች። ፍራንስዋ ቶምቦልባይ የአገሪቱ የመጀመሪያው ፕሬዚደንት ሆኑ።
  • ፲፱፻፺፭ ዓ/ም - የፓሪስ ከተማ የሙቀት ሞገድ እስከ አርባ አራት ዲግሪ ሴልሲዩስ ደርሶ ባስከተለው ሰበብ ወደ መቶ አርባ አራት ያህል ሰዎች ሞቱ።

ልደት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ዕለተ ሞት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ዋቢ ምንጮች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]