Jump to content

ኒኑርታ-አፒል-ኤኩር

ከውክፔዲያ

ኒኑርታ-አፒል-ኤኩር1198 ዓክልበ. እስከ 1186 ዓክልበ. ድረስ የአሦር ንጉስ ነበረ።

የአሦር ነገሥታት ዝርዝር ቅጂዎች ግን ስለ ዘመኑ መጠን ይለያያሉ፤ አንዳንድ እንደሚለው ለ13 ዓመት ሳይሆን ለ3 አመት ብቻ ነገሠ። ባለፈው ቅርብ ጊዜ ግን ለዚሁ ዘመን ተጨማሪ የአመት ስሞች ለሥነ ቅርስ ስለ ተገኙ፣ 13 ዓመት ትክክለኛ እንደ ሆነ ታውቋል።[1]

ዝርዝሩ ስለእርሱ «የኢላ-ሐዳ ልጅ፤ የ1 ኤሪባ-አዳድ ተወላጅ፣ ወደ ካርዱንያሽ ሄደ፤ ከካርዱንያሽም ወጥቶ ዙፋኑን ቀማ» ይላል። አባቱ ኢላ-ሐዳ በ3 አሹር-ኒራሪ ዘመን የሓኒጋልባት (ሚታኒ) አገረ ገዥ ሆኖ ነበር። ዙፋኑን የቀማው ከኤንሊል-ኩዱሪ-ኡጹር ሲሆን በካሳውያን እርዳታ እንደ ተደረገ ይመስላል።

በአንድ ጽላት ዘንድ፣ የካርዱንያሽ (ባቢሎን) ንጉሥ መሊ-ሺፓክ ለኒኑርታ-አፒል-ኤኩር የፈረስ ቡድኖችና ምንጣፎች እንደ ስጦታ ላከው። [2]

በኒኑርታ-አፒል-ኤኩር ዘመን ደግሞ (በ1195 ዓክልበ. ገደማ)፣ አንድ የምድር መንቀጥቀጥአሹር ከተማ የነበረውን አረመኔ ቤተ መቅደስን በሙሉ አጠፋው።

ከርሱ ዘመን በኋላ፣ ልጁ 1 አሹር-ዳን የአሦር ንጉሥ ሆነ።

  1. ^ Jaume Llop: MARV 6, 2 und die Eponymenfolgen des 12. Jahrhunderts. In: Zeitschrift für Assyriologie. 98, 2008, ገጽ. 20–25. (ጀርመንኛ)
  2. ^ የቅርቡ ስነ ቅርስ ውጤቶች (እንግሊዝኛ)
ቀዳሚው
ኤንሊል-ኩዱሪ-ኡጹር
የአሦር ንጉሥ ተከታይ
1 አሹር-ዳን