Jump to content

አምልኮ

ከውክፔዲያ

አምልኮ ወይም አምልኮት የሚለው ቃል "መለክ" ማለትም "መገዛት" ከሚል የግዕዝ ቃል የሚመነጭ ሲሆን በሙሉ ሁለንተና የሚቀርብ ልመና፣ ስእለት፣ ማጎብደድ፣ መተናነስ፣ ስግደት፣ መገዛት ፣ አገልግሎት ማለት ነው። መለኮት በባሕርይ የበላይና ገዢነትን ስለሚያመለክት ለሰውና ለፍጡር አይሆንም። ዕብራውያን /ኤል/ ወይም /ኤሎሃ/ የሚሉትን አረቦች /ኢላህ/ ይላሉ። ሁሉም የመለኮት ሥልጣን ያሳያል። በዚህ መልክ ከሄድን ከፈጣሪ ውጪ የማምክ ተግባር የጣዖት አምልኮ ይባላል።

«አምልኮ» የሚለው ቃል በእብራይስጥ /አባድ/ עָבַד ሲሆን በግሪክ ደግሞ /ላትሬኦ/ λατρεύω ነው፤ ይህም ለአንዱ አምላክ ብቻ በሙሉ ሁለንተና የሚቀርብ ልመና፣ ስእለት፣ ማጎብደድ፣ መተናነስ፣ ስግደት፣ መገዛት ፣ አገልግሎት (Adoration፣ worship) ነው፤ ይህም አምልኮ ለአንድ አምላክ ብቻ እንደሚገባ የመለኮታዊ ትምህርት ቅሪት ባለበት ባይብል ላይ ሰፍሯል፦

  • ዘዳግም 6፥13 አምላክህን ያህዌህን ፍራ እርሱንም #አምልክ תַעֲבֹ֑ד በስሙም ማል።
  • ዘዳግም 10፥20 አምላክህን ያህዌህን ፍራ፥ እርሱንም #አምልክ תַעֲבֹ֑ד ከእርሱም ተጣበቅ፥ በስሙም ማል።
  • ዘዳግም 13፥4 አምላካችሁን ያህዌህን ተከተሉ፥ እርሱንም ፍሩ፥ ትእዛዙንም ጠብቁ፥ ቃሉንም ስሙ፥ እርሱንም תַעֲבֹ֑ד፥ ከእርሱም ጋር ተጣበቁ።
  • ኢያሱ 24፥14 አሁንም ያህዌህን ፍሩ፥ በፍጹምም በእውነተኛም ልብ #አምልኩት תַעֲבֹ֑ד አባቶቻችሁም በወንዝ ማዶ በግብፅም ውስጥ ያመለኩአቸውን አማልክት ከእናንተ አርቁ፥ ያህዌህንም አምልኩ תַעֲבֹ֑ד ።
  • ሳሙኤል ቀዳማዊ 12፥20 ሳሙኤልም ሕዝቡን አለ። አትፍሩ በእውነት ይህን ክፋት ሁሉ አደረጋችሁ ነገር ግን ያህዌህን በፍጹም ልባችሁ #አምልኩት תַעֲבֹ֑ד እንጂ ያህዌህን ከመከተል ፈቀቅ አትበሉ።
  • ሳሙኤል ቀዳማዊ 7፥3 ሳሙኤልም የእስራኤልን ቤት ሁሉ። በሙሉ ልባችሁ ወደ ያህዌህ ከተመለሳችሁ እንግዶችን አማልክትና አስታሮትን ከመካከላችሁ አርቁ፥ ልባችሁንም ወደ ያህዌህ አቅኑ፥ እርሱንም ብቻ #አምልኩ תַעֲבֹ֑ד… ብሎ ተናገራቸው።
  • ማቴዎስ 4፥10 ያን ጊዜ ኢየሱስ፦ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ #አምልክ λατρεύσεις ተብሎ ተጽፎአልና አለው።

ልብ አድርግ አንድ ማንነት ብቻ ያለው አንድ አምላክ መሆኑን ለማመልከት «እርሱን» ብቻ አምልክ በሚል በገላጭ (adjective) የተጠፈነገ ነጠላ ተውላጠ ስም እንጂ «እነርሱ» የሚል የለም፤ ታዲያ ሶስት ማንነቶች ያሉባቸውን ምስልና ሃውልት አበይት በሚባሉት በኦርቶዶክስ፣ በካቶሊክ እና በአንግሊካን አብያተ-ክርስቲያናት ለምን ይሰገዳል፣ እጣን ይጨሳት፣ ይሸረገዳል፣ ይጎባደዳል? ይህ የጣኦት አምልኮ ካልሆነ ምን እንበለው? ወገኖቻችን፦ “ለስእልና ለሃውልት የአምልኮ ስግደት ሳይሆን የፀጋ ስግደት ነው የምናደርሰው” ይላሉ፤ እርግጥ ነው የአክብሮት ስግደት ባይብል ላይ ለመላእክትና ለሰዎች አይተናል፤ ግን የት ቦታ ነው ለማይሰማና ለማይለማ ምስልና ሃውልት ስገዱ የተባለው? ከዚያ ይልቅ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ፤ አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም ተብሏል፦

  • ዘጸአት 20፥4 በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ፤ #አትስገድላቸው፥ #አታምልካቸውምም፤

የሚገርመ የአገራችን ሰዎች እንዲህ ይፀልያሉ፦ “ዓለምን ለማዳን ሲል ኢየሱስ ክርስቶስ “ለ”ተሰቀለበት [[መስቀል]ም እስገዳለው” የዘወትር ጸሎት «መስቀል» እንጨት፣ ብር፣ ወርቅ ወይም ብረት አይደለምን? ይህንን ቀርፆ ለእርሱ መስገድ የጣኦት ክፍል አይደለምን? ሥላሴን በጀሶ ቀርፆ ወደ እነርሱ አምላኬ እያሉ መለማመን ባእድ አምልኮ አይደለምን?

  • ኢሳይያስ 44፥17 #የቀረውንም #እንጨት አምላክ አድርጎ ምስል ይቀርጽበታል፤ በፊቱም ተጐንብሶ #ይሰግዳል ወደ እርሱም #እየጸለየ፦ አምላኬ ነህና አድነኝ ይላል።
  • ኢሳይያስ 45፥20 እናንተ ከአሕዛብ ወገን ሆናችሁ ያመለጣችሁ፥ ተሰብስባችሁ ኑ በአንድነትም ቅረቡ፤ #የተቀረጸውን #የምስላቸውን #እንጨት የሚሸከሙና ያድን ዘንድ ወደማይችል አምላክ #የሚጸልዩ እውቀት የላቸውም።
  • ኤርምያስ 10፥2-5 ያህዌህ እንዲህ ይላል፦ “የአሕዛብን መንገድ አትማሩ ከሰማይ ምልክትም አትፍሩ፤ አሕዛብ ይፈሩታልና። “የአሕዛብ ልማድ” ከንቱ ነውና፤ ዛፍ ከዱር ይቈረጣል፥ በሠራተኛም እጅ በመጥረቢያ ይሠራል። በብርና በወርቅ ያስጌጡታል፥ እንዳይናወጥም በችንካርና በመዶሻ ይቸነክሩታል። እንደ #ተቀረጸ ዓምድ ናቸው እነርሱም አይናገሩም፤ መራመድም አይቻላቸውማን ይሸከሙአቸዋል። ክፉ መሥራትም አይቻላቸውምና፥ ደግምም መልካም ይሠሩ ዘንድ አይችሉምና አትፍሩአቸው።

የሥላሴ፣ የመላእክት፣ የቅዱሳን ምስልና ሃውልት ክፉ መሥራትም አይቻላቸውም፤ ደግምም መልካም ይሠሩ ዘንድ አይችሉም፤ ካልቻሉ ለምን ይሰገድላቸዋል? ይህ የእኛ የሙስሊሞች ጥያቄአችን ብቻ ነው እንጂ ነቀፌታ ወይም መዘርጠጥ አይደለም፤ አላህ ከእርሱ ሌላ ሰዎች የሚያመልኩአቸውን ጣዖታት አትስደቡ ብሎናል፤ ምክንያቱም ድንበርን በማለፍ ያለእውቀት አላህን ይሰድባሉና፦ 6፥108 እነዚያንም ከአላህ ሌላ “የሚጠሩዋቸውን” يَدْعُونَ ጣዖታት አትስደቡ፤ ድንበርን በማለፍ ያለእውቀት አላህን ይሰድባሉና። وَلَا تَسُبُّوا۟ ٱلَّذِينَ يَدْعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ فَيَسُبُّوا۟ ٱللَّهَ عَدْوًۢا بِغَيْرِ عِلْمٍۢ

“ዒባዳ” عبادة የሚለው ቃል “ዓበደ عَبَدَ “አመለከ” ከሚል ግስ የተገኘ ሲሆን “አምልኮ” ማለት ነው፤ አምልኮ የሚገባው አንዱ አምላክ አላህ ብቻ ነው፤ መልእክተኞችም የተላኩበት ጭብጥ ይህ ነው፦ 16:36 በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ “አላህን #አምልኩ اعْبُدُوا፤ ጣዖትንም ራቁ” በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል፤ 21:25 ከአንተ በፊትም፣ እነሆ “ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና #አምልኩኝ فَاعْبُدُونِ ” በማለት ወደ እርሱ የምናወርድለት ቢሆን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም።

ለናሙና ያክል እነዚህ መልእክተኞች፦ ኑሕ 23:23 ኑሕንም ወደ ሕዝቦቹ በእርግጥ ላክነው፡፡ ወዲያውም «ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን #አምልኩ اعْبُدُوا፡፡ ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም፡፡ አትጠነቀቁምን» አላቸው፡፡

ሁድ 11:50 ወደ ዓድም ወንድማቸውን ሁድን ላክን አላቸው ፦ ወገኖቼ ሆይ አላህን #አምልኩ اعْبُدُوا ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም፤ እናንተም ቀጣፊዎች እንጂ ሌላ አይደላችሁም።

ሷሊህ 7:73 ወደ ሠሙድም ወንድማቸውን ሷሊህን ላክን፤ አላቸው ፦ ወገኖቼ ሆይ! አላህን #አምልኩ اعْبُدُوا ፤ ከርሱ ሌላ ለናንተ ምንም አምላክ የላችሁም፤

ኢብራሂምን 29:16 ኢብራሂምንም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ አስታውስ፦ አላህን #አምልኩ اعْبُدُوا፤ ፍሩትም፤ ይሃችሁ የታውቁ ብትሆኑ ለናንተ በላጭ ነው።

ሹዐይብ 11:84 ወደ መድየንም ወንድማችውን ሹዐይብን፣ ላክን፤ አላቸው ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን #አምልኩ اعْبُدُوا፤ ከርሱ ሌላ ለናንተ አምላክ የላችሁም፤

ሙሳ 2:83 የእስራኤል ልጆችንም ጥብቅ ኪዳን አላህን እንጂ ሌላን #አታምልኩ لَا تَعْبُدُون ፤ … በማለት በያዝንባቸው ጊዜ አስታውሱ፡፡

ዒሳ 5:72 አልመሲሕም አለ፦ የእስራኤል ልጆች ሆይ! ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን #አምልኩ” اعْبُدُوا፤

ነብያችን 11:2 እንዲህ #በላቸው ፦ አላህን እንጂ ሌላን #አታምልኩ أَلَّا تَعْبُدُوا፤ እኔ ለእናንተ ከእርሱ የተላክሁ አስስጠንቂ እና አብሳሪ ነኝ።

ቁርአን ሲሶው የሚናገረው ስለ ኢባዳ ነው፣ ይህ የቁርአን አንድ ሶስተኛው የአምልኮ ጭብጥ በቀድሞዎቹ መጻሐፍት ውስጥ የተወሳ ነው፣ ለቀድሞቹ ነቢያት የመጣው የተውሂድ ትምህርት ነው በቁርአን ውስጥ የመጣው፣ በፊት ለነበሩት መልክተኞች የተባለው “አምልኩኝ” ሲሆን በነብያችን የተባለው ይህ ነው፤ ይህ ለእሳቸው እና ከእሳቸው በፊት የነበረው የተውሒድ መገሰጫ ነው፦ 26:196 እርሱም ቁርኣን በቀድሞዎቹ መጻሐፍት ውስጥ “የተወሳ” ነው፡፡ 23:68 የቁርኣንን ንግግሩንም አያስተነትኑምን ወይስ ለመጀመሪያዎቹ አባቶቻቸው ያልመጣ ነገር መጣባቸውን? 41:43 ከአንተ በፊት ለነበሩት መልክተኞች የተባለው “ቢጤ” እንጅ ለአንተ ሌላ አይባልም፤ 21:24 ይልቁንም ከእርሱ ሌላ አማልክት ያዙን? አስረጃችሁን አምጡ፤ *ይህ እኔ ዘንድ ያለው መገሠጫ፣ ከኔ በፊትም የነበረው መገሠጫ ነው* በላቸው። በእውነቱ አብዛኞቻቸው እውነቱን አያውቁም፤ ስለዚህ እነርሱ እንቢተኞች ናቸው أَمِ ٱتَّخَذُوا۟ مِن دُونِهِۦٓ ءَالِهَةًۭ ۖ قُلْ هَاتُوا۟ بُرْهَٰنَكُمْ ۖ هَٰذَا ذِكْرُ مَن مَّعِىَ وَذِكْرُ مَن قَبْلِى ۗ بَلْ أَكْثَرُهُمْ لَا يَعْلَمُونَ ٱلْحَقَّ ۖ فَهُم مُّعْرِضُونَ ። Or, have they taken gods besides Him? Say: Bring your proof; this is the reminder of those with me and the reminder of those before me. Nay! most of them do not know the truth, so they turn aside. Shakir translation

በቀድሞዎቹ መጻሐፍት ውስጥ ፈጣሪ “ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ” ብሎ የተናገረ አምላክ ዛሬም በዘመናች እኔን ብቻ አምልኩ ብሎ በተከበረው ቃሉ ይናገራል፦ 29:56 እላንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፤ እኔንም ብቻ #አምልኩኝ فَاعْبُدُونِ ። 24:55 በእኔ ምንንም የማያጋሩ ሆነው #ያመልኩኛል يَعْبُدُونَنِي ፤ ከዚያም በኋላ የካደ ሰው እነዚያ እነርሱ አመጠኞች ናቸው። 51:56 ጋኔንንና ሰውን #ሊያመልኩኝ لِيَعْبُدُونِ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም። 21:92 ይህች ሕግጋት አንዲት መንገድ ስትኾን በእርግጥ ሃይማኖታችሁ ናት፤ እኔም ጌታችሁ ነኝና #አምልኩኝ فَاعْبُدُونِ ። 6:102 ይህ ጌታችሁ አላህ ነው፡፡ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፡፡ ነገርን ሁሉ ፈጣሪ ነው፡፡ ስለዚህ #አምልኩት فَاعْبُدُوهُ ፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነው፡፡

: