አርጎባ

ከውክፔዲያ

አርጎባ ኢትዮጵያ በደቡብ እስከ ባሌ በምስራቅ እስከ ሐርርአፋር ሰሜን ወሎ ትግራይ ክፍል ድረስ የሚኖሩ አርጎብኛ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎችን የሚገልጽ ቃል ነው።

አርጎባ በአፋር ዞን 3 የአርጎባ ልዩ ወረዳ፣ አዋሽ ሠባት ኪሎ፣ ወረርና የመሳሰሉት፣ በአማራ ሰሜንሸዋ (ምንጃር - መልካጅሎ፣ ጮባ፣ በረኸት፣ አሳግርት፣ ሸዋ ሮቢት፣ አጣዬ፣ ጣርማበርና የመሳሰሉት፣ በደቡብ ወሎ ዞን ምስራቃዊ ክፍሎች፣ ቃሉና አካባቢውእና ኦሮሚያ ልዩ ዞን እንዲሁም በኦሮሚያና ሀረሪ ክልሎች በስፋት ይኖራሉ።

አርጎባ የሚለው ስያሜ «በወቅቱ የነበሩ አፄዎች አረብ ገባ ብለው የአርጎባ ማህበረሰብን መጠርያ ከአርጎባ ጋር ያያልዙታል። ይህ የብሄረሰቡ ትክክለኛ መጠርያ ሳይሆን ሊሉ የፈለጉት ውጫዊ ናቸው ለማለት ነው። አርጎባዎች  መቶ በመቶ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ናቸው። በእርሻንግድና በሽመና ይተዳደራሉ። ኢትዮጵያ ይኖር የነበረ ጥንታዊ ህዝብ ነው።

በተለይ በ13ኛው እና በ14ኛው ክፍለ ዘመንየወላሽማ ስርወ መንግስትን ማለትም የይፋት ወላስማ ሥርወ መንግስት እና የአደል ወላስማ ስርወ መንግስት ያስተደደረ ንግድን መስርቶ ይኖር የነበረ በኢትዮጵያ የመጀመርያውን እስላማዊ መንግስትን የመሰረተ ከዚያም በሁለተናዉ ሂጅራ በነብዩ መሃመድ የእስልምና እምነት ተከታዮች ከቁርሾች ጋር በነበረው ግጭት ወደ ኢትዮጵያ የገቡ አረቦችን ተቀብሎ ያስተናገደ ሃይማኖታቸውንም የተቀበለ የኢትዮጵያ የመጀመርያው የሙስሊም ማህበረሰብ ነው ማለት ይቻላል።

የአርጎባ ህዝብ ባህላዊ እና መንፈሳዊ መሪዎች አሉት፦ ሱልጣን፣ ጋራድ፣ ኢማም፣ አሚር፣ ወዚር፣ ቃዲ፣ ሸህ፣ አባ ጋር፤አባዬ፤አቦኝ… የሚባሉ የሽማግሌዎችና የወጣቶች መሪዎች አሉት።