Jump to content

አርጎብኛ

ከውክፔዲያ

አርጎብኛደቡባዊ ሴሜቲክ ቋንቋዎች አንዱ ነው። በአንድ ወገን በጥቂቱ ከዐማርኛ በሌላ ወገን ከሐረርኛ ጋር ተመሳሳይ ቅርጽ ያለው ቋንቋ ነው።

አርጎባ ማኅበረሰብ፣ በኢትዮጵያ በሰሜናዊ ክፍል ትግራይወሎ፣ በደቡብ እስከ ባሌ ፣ በምሥራቅ እስከ ሐረር ቆላማ ስፍራና አፋርሰሜን ሸዋ አካባቢ የሚኖሩ ሕዝቦች ናቸው፡፡

አርጎባዎች በኤርትራም እንደሚኖሩ ሲጠቆም «ጀበርት» የሚል መጠሪያ አላቸው፡፡ «አርጎባ» የብሔረሰብ እና የቋንቋ መጠሪያ ነው። በ13ኛው ክፍለ ዘመንየወላስማ ሥርወ መንግሥት [የይፋት ወላስማ እና የአደል ወላስማ ስርወ መንግስትን ከመነሻው የሸዋ ሱልጣኔት 896 ጀምሮ ከ1108 አካባቢ ጀምሮ የተስፋፋ ከ1285 እስከ 1559 እኤአ ድረስ ያስተዳደረ ] ንግድን መሥርቶ በነበረ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን እስላማዊ መንግሥትን እንዳቋቋመ የሚገለጸው ፤በሁለተኛው ሂጅራነብዩ መሐመድእስልምና እምነት ተከታዮች ከቁረሾች ጋር በነበረው ግጭት ወደ ኢትዮጵያ የገቡ አረቦችን ተቀብሎ ያስተናገደ የመጀመሪያው የሙስሊም ማህበረሰብ የአርጎባ ማህበረሰብ እንደሆነም ይጠቁማሉ። ከወላስማ ሱልጣኔት መፍረስ ጀምሮ እየተዳከመ እና ከኢማም አህመድ ሞት ቡሃላ የተበታተነ ህዝብ ነው። ሰለሞናዊው ሥርወ-መንግሥትኢትዮጵያ የቀድሞ ሥርወ-መንግሥት ነበረ። የወላስማ ስርወ መንግስት ከ1285 –1559:1577 ቢዳከምም እስከ 1680ዎቹ ድረስ ከሰለሞናዊያን ጋር በሃይማኖት ልዩነቶች በፈጠሩ አለመግባባቶች በጦርነቶች የግዛት ክልላቸው ሲሰፋና ሲጠብ ኖሯል። ሰለሞናዊው ሥርዎ መንግሥት በኢትዮጵያ 1270 አንስቶ እስከ 1966 ዓ.ም. ያለውን ጊዜ ወይም እስከ ሐይለ ሥላሤ ቀዳማዊ ንጉሠ፦ነገሥት ዘኢትዮጵያ እስከ ወደቁበት ጊዜ የሚመለከት ነው። በአሁኑ ደግሞ በአፋር ክልል አርጎባ ልዩ ወረዳ ከ1989አም ጀምሮ እና በአማራ ክልል አርጎባ ልዩ ወረዳ በ1998አም ጀምሮ ተቋቁሞ ራሱን በራሱ በከፊል እያስተዳደረ ይገኛል።

«አርጎብኛ» የሴሜቲክ ቋንቋ ዝርያ ሲኾን በውል የተለዩ ኹለት ዘዬዎች አሉት። የመጀመሪያው በደቡብ ወሎ አካባቢ የሚነገረው «ሾንኬ ጦልሃ» እና በአፋር ክልል አርጎባ ልዩ ወረዳና በሰሜን ሸዋ የሚነገረው «ሸዋ ሮቢት ልዩ አምባ ዘዬ» በመባል ይታወቃሉ።

ከሰሜን እስከ ደቡብ ምስራቅ ተበታትነው በስብጥርና በኩታገጠምነት የሚገኙት አርጎባዎች ሙሉ በሙሉ የእስልምና እምነት ተከታዬች ሲኾኑ «አርጎባ» የሚለው የብሔረሰቡ መጠሪያ ስያሜ እንደ አካባቢው ነዋሪዎች እምነት የአፄው መንግስት እስልምን ላለመደገፍ… «አረብ ገባ» ለማለት የተፈለገ ነው።

እንደ ጥናቶች ግን «የአርጎባ ሕዝብ በኢትዮጵያ ይኖር የነበረ ጥንታዊ ሕዝብ መኾኑንና ከዚህ በፊት የተለያዩ ስያሜዎች እንደነበሩትና እስልምናን በተለያዩ ጊዜዎች የተቀበለ ያስፋፋ ኅብረተሰብ ነው» በሚል ይገለጻል። ነገር ግን በሚኖሩባቸው የተለያዩ አካባቢዎች አኹን የሚገኙት የብሔረሰቡ አባላቶች የተለያዩ የብሔሩ ጎሳዎች ጋር ትስስር ያላቸው የአረባዊ የዘር ሐረግ ያለቸው እንዳሉም ታሪክ ያስረዳል።

የአርጎባ ማኅበረሰብ መተዳደሪያው ከኾነው ንግድ፣ ዕርሻና የሽመና ሥራ ከኢትዮጵያ የመን ድረስ በመጓጓዝ ትስስሩ በጋብቻም ተዋልደዋል። በአርጎባዎች በሚኖሩበት አካባቢ የልጅ ልጆቻቸው ይገኛሉ።

አርጎብኛ ከቋንቋው በተጨማሪ የማኅበረሰቡ መገለጫ የኾኑ የሰርግ፣ የሐዘን፣ የአመጋገብ ስርዓቶቻቸው፣ ለቱሪስት መስህብነት ከፍተኛው ድርሻ ያለው ሲኾን የተለየ ጥበብ ያረፈባቸው እና ከአንድ ሺህ ዓመት በላይ ያስቆጠሩ የመኖሪያ ቤቶች፣ መስጊዶቻቸው ባህላዊ የሥነ ጥበብ ሕንጻ ውበት ጥንታዊውን ፣ የታሪክ ፣ የቋንቋ ፣ የእምነት ፣ የአኗኗር ፍልሥፍና የሥልጣኔ ዘመን ያስታውሳሉ።

የቋንቋውን ይዘት አጠቃላይ ገጽታ እላይ እሚታየው መልመጃ ገጽ ላይ ወየም እዚህ [1] በመጫን መቃኘት ይችላሉ።