ኡሰርካሬ ኸንጀር

ከውክፔዲያ
ኡሰርካሬ ኸንጀር
በኸንጀር ሀረም ውስጥ የተገኘው የኸንጀር ሀረም ምስል
በኸንጀር ሀረም ውስጥ የተገኘው የኸንጀር ሀረም ምስል
የግብጽ ፈርዖን
ግዛት 1774-1766 ዓክልበ. ግ.
ቀዳሚ ኹታዊሬ ወጋፍ
ተከታይ ስመንኽካሬ ኢሚረመሻው
ባለቤት ሰነብኸናስ
ሥርወ-መንግሥት 13ኛው ሥርወ መንግሥት

ኡሰርካሬ ኸንጀር ላይኛ ግብጽ2ኛው ጨለማ ዘመን (13ኛው ሥርወ መንግሥት) ከ1774 እስከ 1766 ዓክልበ. ግድም ድረስ የገዛ ፈርዖን ነበረ። ምናልባት የኹታዊሬ ወጋፍ ተከታይ ነበረ።

ቶሪኖ ቀኖና ነገሥታት ዝርዝር ላይ «ኡሰር<..>ሬ <...>ጀር» ይገኛል። በመምኅር ኪም ራይሆልት አስተሳሰብ፣ «ኸንጀር» የሚለው ስያሜ ግብጽኛ ሳይሆን በአንዳንድ ሴማዊ ቋንቋዎች «እሪያ» ማለት ሊሆን ይችላል። ስለዚህ ሴማዊው ፲፬ኛው ሥርወ መንግሥት በጌሤም እየገዛ ምናልባት የሴማውያን ተጽእኖ በጤቤስ መንግሥት ደግሞ በዚህ ሊታይ ይችላል።

ኸንጀር በተለይ ስላሠራው «የኸንጀር ሀረም» ይታወቃል። በዚህ ሀረም በሁለት ድንጋዮች የኸንጀር ፩ኛው ዓመትና የ፭ኛው ዓመት ዘመነ መንግሥት ተመዘገበ። ስለዚህ ብዙ ሊቃውንት ከ፭ ዓመታት በላይ እንደ ገዛ አያምኑም።

በዚህ ዘመን «ኦሩስ፣ አኸንኸሬስ፣ አኮሪስ፣ ኸንክሬስ፣ አኸሬስ» በግብጽ እንደ ገዙ በአንዳንድ ምንጭ ይገኛል። እነዚህ ስሞች ሆር አዊብሬሰኸምሬኹታዊ ኻውባውሰጀፋካሬ፣ ኸንጀር፣ እና ስመንኽካሬ ቢመስሉም፣ ከማኔጦን ጀምሮ ስሞቻቸው ከ፲፱ኛው ሥርወ መንግሥት ፈርዖኖች ጋር እንደ ተዛቡ ይመስላል። «ኸንክሬስ» የ፰ ወይም ፲፪ ዓመታት ዘመን እንደ ነበረው ይባላል። በአንዳንድ የድሮ ምንጭ ደግሞ «ኸንክሬስ» በዘጸአት ዘመን የጠፋው ፈርዖን ሲባል ይህ ደግሞ እንደ ተዛበ ይመስላል።

በኸንጀር ዘመን ጠቅላይ ሚኒስትሩ («ጨቲ» የሚባለው ሹመት) አንኹ እንደ ነበር ይታወቃል። የአንኹ ቤተሠብ ኃይለኛ ሹሞች ነበሩ፣ አባቱ ዛሞንት3 አመነምሃት ዘመን ጨቲ ሲሆን የአንኹ ሁለት ወንድ ልጆች ረሠነብና ኢይመሩ በኋላ ጨቲዎች ሆኑ። ይህም አንኹ ደግሞ በኻአንኽሬ ሶበክሆተፕ (1795-1791 ዓክልበ. ግ.) ጨቲ መሆኑ ታውቋል፤ ስለዚህ አንኹ ምናልባት ከኻአንኽሬና ከኸንጀር መካከል ለገዙት ፈርዖኖች ለሁላቸው እንደ ጨቲ ያገልግል ነበር። እንዲህ ከሆነ፣ በዚህ ዘመን ጨቲው እውነተኛው ባለሥልጣን ሲሆን ፈርዖኖች ግን ድካሞችና በቶሎ የሚተኩ እንደ ነበሩ ይመስላል።

ቀዳሚው
ኹታዊሬ ወጋፍ
ግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን
1774-1766 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ስመንኽካሬ ኢሚረመሻው

ዋቢ ምንጭ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  • K.S.B. Ryholt: The Political Situation in Egypt during the Second Intermediate Period, c. 1800 – 1550 BC, Carsten Niebuhr Institute Publications, vol. 20. Copenhagen: Museum Tusculanum Press, 1997 (እንግሊዝኛ)