የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በሀገሪቱ ውስጥ ከፍተኛው የስፖርት ክንውን ነው። ይህ ሊግ በየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስር የሚተዳደር ሲሆን በየጊዜው የተለያዩ ስፖንሰሮች ደግፈውታል። ሊጉ በየ አመቱ የሚከናወን ሲሆን በ አመት ውስጥ በሁለት ክፍል (ሲዝን) ተከፍሎ ይካሄዳል። ሊጉን ለማሸነፍ አንድ ክለብ ከፍተኛ ነጥብ ይዞ አመቱን መጨረስ ይጠበቅበታል። ክለቦች እርስ በእርሳቸው በአመት ሁለት ጊዜ ይገናኛሉ። እያንዳንዱ ክለብ አንድ ጨዋታ በ ራሱ ሜዳ ሌላውን በባላጋራ ክለብ ሜዳ ያከናውናል።

Ann.jpg

ታሪክ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የኢትዮጲያ ፕሪሚየር ሊግ የተመሰረተው በ 1994 ዓ.ም. ነው። የሊጉ አርማ ከዚህ በላይ የሚገኘው ነው። ይህ ሊግ በ እ.አ.አ.2009/10 የውድድር ዘመን በ 18 ክለቦች እየተከናወነ ነው። የሊጉ ችግሮች ተብለው ከጠቀሱት መካከል አብዘሃኛው ጨዋታዎች በአዲስ አበባ ስታዲየም መካሄዳቸው ነው። ይህን ችግር ለመቅረፍ ይመስላል የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ የራሱን ስታዲየም በ ዶ/ር ሼህ መሀመድ ሁሴን አሊ አላሙዲ እና በደጋፊው መዋጮ የራሱን ስታዲየም በማስገንባት ላይ ነው። ይህ ሊግ በ እ.አ.አ. 2007 ችግር አጋጥሞት ነበር። ለዚህም ቺግር 12 የ ሊጉ ክለቦች ( ሰባቱን የአዲስ አበባ ክለቦች ጨምሮ ማለት ነው። ) ራሳቸውን አግልለው ነበር። በዚህ ጊዜ ፌዴሬሽኑ ዋንጫውን ለ ሃዋሳ ከነማ ክለብ ሰጥቷል። ኢትዮጵያ በ አለም አቀፉ የ እግር ኳስ ማህበር ፊፋ እስከመታገድ የደረሰችበት ጊዜ ነበር። ይህ እገዳ ከብዙ አለም አቀፍ ውድድሮች እንድትታገድ ያደረጋት ሲሆን እገዳው በቅርቡ ተነስቶላታል። ሊጉ በአሁኑ ሰአት በቀድሞው አመራሮች መመራቱ ቀርቶ በ አዲስ አመራሮች መመራት ጀምሯል።

ከፍተኛ ግብ አግቢዎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

2007/8 ሳልሃዲን ሰይድ በተጠቀሰው አመት ከፍተኛ ግብ አግቢ ሁኖ ጨረሰ። ያገባቸው ጎሎች ብዛት 21 ነው። ተጫዋቹ የቅዱስ ጊዮርጊስ የእግር ኳስ ክለብ ተጫዋች ነው።

ብዙ ጊዜ ማሸነፍ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ሊጉን በተደጋጋሚ በማሸነፍ ደረጃውን የያዙት ክለቦች የሚከተሉት ናቸው፡

  • 20 (ሃያ) ጊዜ..............................ቅዱስ ጊዮርጊስ የእግር ኳስ ክለብ
  • 6 (ስድስት) ጊዜ..........................መቻል የእግር ኳስ ክለብ
  • 5 (አምስት) ጊዜ..........................ጦር የእግር ኳስ ክለብ

አሸንፈዋል።

ጦር የእግር ኳስ ክለብ እ.አ.አ. ከ 1951 እስከ 1954 በተከታታይ 4 (አራት) ጊዜ በማሸነፍ ታሪክ ያለው ክለብ ነው። ይህ ክለብ በአሁኑ ጊዜ የለም። አሁን ካሉት ክለቦች ደግሞ ቅዱስ ጊዮርጊስ የእግር ኳስ ክለብ እ.አ.አ. ከ 1994 እስከ 1996 በተከታታይ ለ3 (ሶስት) ጊዜ ያህል በማሸነፍ ብቸኛው ክለብ ነው። በደጋፊ ብዛትም ቢሆን ብልጫውን እንደሚይዝ ብዙዎች ይናገራሉ።

ድረ ገጽ ያላቸው[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ክለቦች የራሳቸው የድረ ገጽ አድራሻ ያላቸው ክለቦች 2 (ሁለት) ብቻ ናቸው። እነርሱም፡ ኢትዮጵያ ቡና የእግር ኳስ ክለብ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ የእግር ኳስ ክለብ ናቸው። እነሱም:- የቅዱስ ጊዮርጊስ (http://www.saintgeorgefc.com/) እንዲሁም የኢትዮጵያ ቡና የእግር ኳስ ክለብ ድረ ገጽ (http://www.ethiopiancoffeesportclub.com/) ናቸው ።

የሊጉ ተሳታፊ ክለቦች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በሊጉ ውስጥ በ፳፻፫ ዓ.ም. የሚሳተፉ ክለቦች 18 (አስራ ስምንት) ናቸው። እነዚህም፦

ደግሞ ይዩ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]