ከምከም
Appearance
(ከከምከም ወረዳ የተዛወረ)
ከምከም በደቡብ ጎንደር ዞን የሚገኝ ወረዳ ነው። የአስተዳደር ማዕከሉ አዲስ ዘመን (ከተማ) ሲሆን ይፋግ እና አምባ ሜዳ የተባሉ ሁለት አንስተኛ ከተማዎችን ያቅፋል።
ርብ እና አርኖ ወንዞች በወረዳው አልፈው ወደ ጣና ሐይቅ የፈሳሉ። ጤፍ፣ ማሽላ፣ በቆሎ፣ ጥጥ እና ሰሊጥ በአካባቢው ይመረታሉ።
እንደ 1999 የሕዝብ ቆጠራ በወረዳው 198,435 ሰዎች ሲኖሩ፤ ከ1986ዓ፣ም. የሕዝብ ብዛት የ 9.97% ቅነሳ አሳይቷል።
ዓ.ም.** | የሕዝብ ብዛት |
---|---|
1986 | 212,341
|
1999 | 198,435
|
- ^ Ethiopia-Sudan Power Systems Interconnection Project, ESIA Final Report, p. 55 (Ethiopian Electric Power Corporation website) This was based on information provided by the woreda in 2006.
- ^ http://www.nai.uu.se/library/resources/dossiers/local_history_of_ethiopia/A/ORTAC05.pdf
- ^ CSA 2005 National Statistics, Table B.4