Jump to content

ኩቲክ-ኢንሹሺናክ

ከውክፔዲያ

ኩቲክ-ኢንሹሺናክ (አካድኛፑዙር-ኢንሹሺናክ) ከ2013 እስከ 1979 ዓክልበ. ግድም ድረስ የአዋን (ኤላም) ንጉሥ ነበረ።

ስሙ በአዋን ነገሥታት ዝርዝር መጨረሻው ሲሆን ዘመኑ በአንዳንድ ቅርሶች ይታወቃል። መጀመርያ በአካድ ንጉሥ ሻርካሊሻሪ ዘመን የሱሳ አገረ ገዥ ነበር። ከሻርካሊሻሪ ዕረፍት በኋላ ግን ብሔራዊ ቀውስ በአካድ ተነሣና ኩቲክ-ኢንሹሺናክ ነጻነት አዋጀ። በአካድ ዘመን የመንግሥት ይፋዊ ቋንቋ አካድኛ ሆኖ ነበር፤ ኩቲክ-ኢንሹሺናክ ግን ኤላምንኛን መለሠ፤ አዲስ ጽሕፈት ደግሞ አስገባ።

በቅርብ ጊዜ ውስጥ የአካድ ኃይል ደከመ፤ ጉታውያን መስጴጦምያን ወረሩ። በሱመር ደቡብ ያሉት ከተሞች ዑርኦሬክላጋሽ ነጻነታቸውን አዋጁ። ኩቲክ-ኢንሹሺናክ በአንድ ዘመቻ ወደ መስጴጦምያ ገብቶ ኤሽኑናንና አካድን ያዘ። በኋላ የላጋሽ ንጉሥ ጉዴአ እና የዑር ንጉሥ ኡር-ናሙ አሸነፉት።

በኩቲክ-ኢንሹሺናክ ዕረፍት ኤላም ለጊዜው በሦስት ክፍሎች (ሱሳ፣ አንሻንሲማሽኪ) ተሰበረ።

ከኩቲክ ኢንሹሺናክ ዘመን የታወቁት ቅርሶች ማሳያ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]