Jump to content

እጸ ፋርስ

ከውክፔዲያ
(ከካናቢስ የተዛወረ)
እጸ ፋርስ

እጸ ፋርስ (Cannabis sativa) ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲሁም በመላው ዓለም የሚገኝ ተክል ነው።

በአንዳንድ ምንጭ ኣጠፋሪስ ወይም አስተናግርት ደግሞ «እጸ ፋርስ» ተብሏል፤ ይህ በፍጹም ሌላ ዝርያ (Datura stramonium) ነው። C. sativa ደግሞ ቃጫ ተብሏል፣ ይህም ለሌላ ዝርያ (Agave sisalana) ይገባል።

የተክሉ ሳይንሳዊ ጸባይ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በብዛት የሚገኝበት መልክዓ ምድር

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
የእጸ ፋርስ ሕግጋት በአሜሪካ አገር (2009 ዓም)

  እጸ ፋርስ አሁን ሕጋዊ የሆነባቸው ክፍላገራት
  እጸ ፋርስ ለሕክምና ሕጋዊ ተደረገ
  አደንዛሽ ያልሆነ እጸ ፋርስ ለሕክምና ተፈቅዷል
  እጸ ፋርስ ተከለክሏል

D እጸ ፋርስ ቅጣት የሌለ ወንጀል ያደረጉት።
v · d · e

በቅርብ ጊዜ ውስጥ አገራት ሕጋዊ እንዲሆን አድርገዋል፤-

ከነዚህ ጭምር ብዙ ሌሎች አገራት አሁን «ቅጣት የሌለ» ወይም «ለሕክምና የተፈቀደ» ወይም በሀገሩ ውስጥ አንዳንድ ክፍላገራት የፈቀዱት አድርገውታል። በኮሎምቢያቺሌጃማይካ አሁን ማረሱም ሕጋዊ ሆኗል።

የተክሉ ጥቅም

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ተክሉ ከጥንት ጀምሮ ቃጫን ስለሚመስለው ስለ ጭረቱ ታርሷል። ይህ ጭረት ጨርቃጨርቅ ወይም ገመድ በመሥራት ጠቃሚ ሆኗል።

ከዚህም በላይ ስለ አደንዛዥነቱ ስለሱስነቱም ከጥንት ታውቋል። ልማዱ ሱስነት ሊሆን የሚችለው እንደ አረቄአፍዮን ወይም ትምባሆ ለሰውነቱ የጥገኝነት ሱስ የሚያምጣ ሳይሆን፣ ለአዕምሮ ሱስ ሊሆን የሚችል ብቻ ነው። (እንዲያም ማናቸውም የሰው ልጅ ተግባር ሲደጋገም የአዕምሮ ሱስ ሊሆን ይችላል፣ ለምሳሌ ሰው ብዙ ጊዜ መዋኛ ቢወድ፣ ወይም ኢንተርኔት መጠቀም፣ ቪዴዎ ጌም ማጫወት ቢሆንም ተግባሩ የአዕምሮ ሱስ ሊሆን ይችላል።)

በ480 ዓክልበ. ግድም የጻፈው ሄሮዶቶስ እንደ መሠከረው፣ እስኩቴስ የተባሉት ሰዎች በጢሱ መተንፈስ ይደሰቱ ነበር። እንዲሁም ከጥንት ጢሱ በሕንድና በቻይና ጥቅም አገኝቷል።

በአንዳንድ ጸሐፊ አስተያየት፣ በብሉይ ኪዳንቅዱስ ዕጣን የተጠቀሰው በዕብራይስጥም «ቅነህ ቦሥም» የተባለው እጽ (ኦሪት ዘጸአት 30:23) በውነት «ካናቢስ» ነበረ። ሌሎች ሊቃውንት ግን ይህን አይቀበሉም፤ በአማርኛም «ጠጅ ሳር» ይላል።

ከ800-950 ዓም በፊት የአረብ ነጋዴዎች ተክሉን «ዳጋ» ተብሎ እስከ ደቡባዊው አፍሪካ ድረስ አስገብተውት ነበር። በላሊበላ ዋሾች የተገኙት ሁለት የካናቢስ ሙጫ ያለባቸው ሸክላ ፒፓዎች ከ1320 ዓም አካባቢ እንደ ነበሩ በትንተና ተረጋግጧል። [1]

እንግሊዞች መጀመርያ በቨርጂኒያ በ1600 ዓም ግድም ሲሠፍሩ የኗሪዎችም ሆነ የኢንግላንድ ካናቢስ አይነቶች ለጭረቱ መተክል በሕግ ግዴታ ሆነ።

20ኛው ክፍለዘመን በብዙ አገራት ክልክል ተደረገ። ይህም በተለይ በጋዜጣዎች ማስፈራራት («ቢጫ ጋዜጠኝነት») ምክንያት ሆነ። አስፈሪ ስም እንዲኖረው በሜክሲካዊ ቅጽል ስሙ ማሪዋና ይሉት ጀመር። በ21ኛው ክፍለ ዘመንሕክምና ጥቅም እንዳለው ሲታወቅ እንዲሁም ለአንዳንድ እምነቶች የመንፈሳዊ ጥቅም እንዳለው ስለሚቆጠር ብዙ አገራት ከትልቅ ወንጄል ደረጃ አቀነሱት ወይም ሕጋዊ አድርገውታል።

  1. ^ ካናቢስ ማጨስ በ14ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ፦ የጥንተ ንጥር ማስረጃ