ክርስቲያን ወጋምቢክ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search
ዶክተር ወጋምቢክ እና ሚስቱ፣ ከደብረ ታቦር ሆስፒታል ፊት ለፊት -- 1961 ዓ.ም.
ስዕል:ወጋምቢክ በደብረ ታቦር አየር ማረፊያ -- 1962 ዓ.ም.

ዶክተር ክርስቲያን ወጋምቢክ (Dr. Kristian Hogganvik) ሃልስኖርዌይ አገር፣ 1903ዓ.ም. በክረምት ወራት (በዚህ ወቅት ፀሐይ ለብዙ ቀናት በኖርዌይ ትደበቃለች) ተወለደ[1]። ቤተሰቦቹ ድሃ የነበሩት ወጋምቢክ 9 ወንድምና እህቶች ነበሩት። ከጫማ ሰሪ አባቱ የእጅ ጥበብን እየቀስመ ቢያድግም በኋላ ላይ ባስየው የአዕምሮ ብሩህነት ከአድቬንቲስት ቤተክርስቲያን ባገኘው የ250 ዶላር (በዓመት) ብድርና ስጦታ እየተረዳ የሕክምና ዲግሪውን እንደጨረሰ የህይወት ታሪኩ ያሳያል[2]

ወጋምቢክ፣ በ1941 ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት የደብረታቦር ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሆስፒታል ህክምና አላፊ፣ ሐኪም እና ቀዶ ጠጋኝ በመሆን ከሚስቱ ጋር ተዛወረ። ለሚቀጥሉት 25 አመታት በዚህ ሆስፒታል ሲያገለግል ወደ ኖርዌይ የተጓዘው ሶስት ጊዜ ብቻ ነበር። ወደ አዲስ አበባም የሚጓዘው በአመት አንድ ጊዜ ለሽርሽር እና የህክምና መገልገያ እቃወችን ለመግዛት ነበር[3]

በወቅቱ፣ ክረምት በመጣ ጊዜ ወደ አዲስ አበባ የሚያገናኘው መንገድ ሙሉ በሙሉ ይቋረጥ ነበር። ስለሆነም የህክምና እቃዎች ለ4ወራት ማግኘት አስቸጋሪ ነበር። ስለሆነም በ1950ዎቹ ይሄው ዶከተር የከተማውን ህዝብ በማስተባበር የደበረታቦር አየር ማረፊያን እንዳቋቋመ የህይወት ታሪኩ ይገልጻል። በ1962 ይሄው የአውሮፕላንም ማረፊያ በሳምንት ሁለት በረራዎችን ያስተናግድ ነበር[4]

ወጋምቢክ የሆስፒታሉን ህንጻ እንዳስፋፋ፣ ሊስተናገዱ የሚችሉ በሽተኞችን ቁጥር እንዳሳደገና የእንጨት ማስተካከያ ማሽኖችን እንደተከለ ታሪኩ ያሳያል። በ1962 ፣ ሚስቱ ሲግኒ፣ አንድ ስዊድናዊት ነርስ እና 17 የአገሩ ሰዎች ይረዱት ነበር። በዚህ ወቅት 3 ልጆች ነበሩት[5]

የአብዮቱን መፈንዳት ተከትሎ ፣ መስከረም 1፣ 1967 ዓ.ም. የደብረታቦር ሆስፒታል ተመዘበረ፤ እንዲሁም የዶክተሩ ቤት በእሳት ተቃጠለ። ወጋምቢክ ወደ አዲስ አበባ በመብረር ያለምንም አደጋ አመለጠ[6]

ከዚህ በኋላ፣ ከአገር በመባረሩ በኖርዌይ አገር ኑሮውን ቀጠለ። በ1987 ዓም የካንሰር በሽታን ሲታገል ቆይቶ በተውለደ በ84 አምቱ በዚያው በኖርዌይ አለፈ።


ማጣቀሻ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ http://www.adventistarchives.org/docs/WM/WM19700601-V79-06__C.pdf, June 1970 (accessed Nov 29,1011)
  2. ^ http://www.adventistarchives.org/docs/WM/WM19700601-V79-06__C.pdf, June 1970 (accessed Nov 29,1011)
  3. ^ http://www.adventistarchives.org/docs/WM/WM19700601-V79-06__C.pdf, June 1970 (accessed Nov 29,1011)
  4. ^ http://www.adventistarchives.org/docs/WM/WM19700601-V79-06__C.pdf, June 1970 (accessed Nov 29,1011)
  5. ^ http://www.adventistarchives.org/docs/WM/WM19700601-V79-06__C.pdf, June 1970 (accessed Nov 29,1011)
  6. ^ http://www.adventistarchives.org/docs/AAR/AAR19751020-V80-42__C.pdf#view=fit