ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/መስከረም 24
Appearance
- ፲፭፻፸፭ ዓ.ም. - የካቶሊኩ ቤተ ክርስትያን ፓፕ ግረጎሪ ፲፫ኛ በኢጣልያ ፤ በፖላንድ ፤ በፖርቱጋል እና በእስፓንያ አገሮች የግሪጎርያዊ ዘመን አቆጣጠርን መሠረተ።
- ፲፭፻፺ ዓ.ም. - የንግሥ ዘመናቸውን (ከ ፲፭፻፶፯ ዓ.ም. እስከ ፲፭፻፺ ዓ.ም.) ሙሉ በቀይ ባሕር በኩል ቱርኮችን (ኦቶማን)፤ በደቡብ የኦሮሞዎችን ጥቃት በመከላከል ያሳለፉት የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ሰርጸ ድንግል በተወለዱ በ ፵፯ ዓመታቸው አረፉ።
- ፲፰፻፲፯ ዓ.ም. - ሜክሲኮ አዲስ ሕገ መንግሥቷን አጽድቃ የፌዴራል ሪፑብሊክ ሆነች።
- ፲፰፻፳፫ ዓ.ም. - ከኔዘርላንድ ጋር በመለያየት የቤልጂግ ሉዓላዊ አገር ተመሠረተ።
- ፲፰፻፵፮ ዓ.ም. - የኦቶማን ግዛት በሩሲያ ላይ ጦርነት አወጀ። ባንድ በኩል ሩሲያ፤ በሌላው በኩል ደግሞ ብሪታንያ፣ ፈረንሳይ እና የኦቶማን ግዛት በትብብር የተዋጉት የሁለት ዓመት በላይ ጦርነት የክራይሚያ ጦርነት የሚባለው ነው።
- ፲፱፻፫ ዓ.ም. - የፖርቱጋል ንጉሥ ማኑዌል ፪ኛ ወደብሪታንያ ኮብልሎ አገሪቱ ሪፑብሊክ ሆነች።
- ፲፱፻፶ ዓ.ም. - ሩሲያ የመጀመሪያዋን ሰው ሰራሽ ሳቴላይት፣ ስፑትኒክ ፩ መሬትን ለመዞር ተኮሰች።
- ፲፱፻፶፱ ዓ.ም. - የብሪታንያ ቅኝ ግዛት የነበረችው፣ በቀድሞ ስሟ ባሱቶላንድ ትባል የነበረችው የደቡባዊ አፍሪካ አካል፣ ነጻነቷን ተቀዳጅታ የሌሶቶ ንጉሥ መንግሥት ተባለች።