ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/መስከረም 29
Appearance
- ፲፰፻፺፱ ዓ.ም. - የሴኔጋል መሪ የነበሩት ሌኦፖልድ ሴዳር ሴንግሆር ተወለዱ።
- ፲፱፻ ዓ/ም - የሐረር ገዥ የነበሩት ደጃዝማች ይልማ መኮንን (የራስ መኮንን የመጀመሪያ ልጅ እና የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ታላቅ ወንድም) አርፈው ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በአባታቸው መቃብር ተቀበሩ።
- ፲፱፻፵፭ ዓ/ም - በታላቋ ብሪታኒያ የኢትዮጵያ አራተኛው ዋና መላክተኛ (Envoy Extraordinary and Minister Plenipotentiary) የነበሩት ሐኪም አዛዥ ወርቅነህ (Dr. Charles Martin) በዚህ ዕለት አረፉ።
- ፲፱፻፶፭ ዓ.ም. - ዩጋንዳ ከብሪታንያ ቅኝ ግዛትነት ነጻነቷን ተቀዳጀች።
- ፲፱፻፷ ዓ.ም. - የአርጀንቲና ተወላጅ የነበረው፤ በአብዮት ቅስቀሳና ፍልሚያ፣ በተለይም በኩባ አብዮታዊ ትግል የሚታወቀው ኤርኔስቶ ጌቫራ በቦሊቪያ የአብዮት ፍንዳታ ሊያንቀሳቅስ ሲሞክር በተያዘ በማግስቱ ተረሽኖ ሞተ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የኢትዮጵያ መንግሥት አልጋ ወራሽ አስፋ ወሰን፣ ሎንዶን በህክምና ሲረዱ ቆይተው፣ ለማገገም በዛሬው ዕለት ወደ ስዊዘርላንድ አመሩ