ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ሰኔ 1
Appearance
- ፲፯፻፸፭ ዓ/ም - በአይስላንድ የሚገኘው ላኪ የተባለው ተራራ በእሳተ ገሞራ ፈንድቶ ከ ፱ ሺ በላይ ሰዎች ሲሞቱ፣ በአገሪቱ ላይ የሰባት ዓመት ረሀብ አስከተለ።
- ፲፰፻፭ ዓ/ም - የሸዋው መርዕድ አዝማች ወሰን ሰገድ አርፈው በቁንዲ ጊዮርጊስ ተቀበሩ። ልጃቸው ንጉሥ ሣህለ ሥላሴ አልጋውን ወረሱ።
- ፲፱፻፳፮ ዓ/ም - በኢጣልያ አስተናጋጅነት የተካሄደው ሁለተኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ውድድር የመጨረሻው ጨዋታ በኢጣልያ እና ቼኮዝሎቫኪያ ቡድኖች ግጥሚያ ሲሆን ኢጣልያ ፪ ለ ፩ አሸንፋ ዋንጫውን ለመጀመሪያ ጊዜ ተቀዳጀች።
- ፲፱፻፴፪ ዓ/ም - የፋሺስት ኢጣልያ ሠራዊት ከደብረ ወርቅ ብዙ ጉዋዝና መሣሪያ ጭኖ ወደ ቢቸና ሲጓዝ የነበላይ ዘለቀ አርበኞች ገጥመውት ከፍተኛ ውጊያ ተደርጎ አርበኞቹ ድል አድርገውት ብዙ መሣሪያ ማረኩ።
- ፲፱፻፷ ዓ/ም - ለአሜሪካ ጥቁሮች ሰብዓዊ መብት ታጋይ የነበሩትን ማርቲን ሉተር ኪንግን የገደለው ጄምስ ኧርል ሬይ በሂዝሮው የሎንዶን አየር ዠበብ ማረፊያ ላይ ተያዘ።